Get Mystery Box with random crypto!

ከ215 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መመዝገባቸውን የአማራ ክልል ት | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

ከ215 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መመዝገባቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ካለፈው ዓመት ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከወትሮው በተለየ መልኩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሰጠት ተጀምሯል፡፡ በአማራ ክልል የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ከ215 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም ድረስ ተካሂዷል፡፡ የተፈታኞች ምዝገባ በትምሕርት ቤቶች በበይነ መረብ ብቻ እንደተካሄደ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተናና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ዝጋለ ማሩ በተለይም ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ውስጥ 579 2ኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የተማሪዎች ምዝገባ ያካሄዳሉ ተብሎ ታቅዶ ነበር ያሉት አቶ ዝጋለ 575 ትምህርት ቤቶች ምዝገባውን ማድረግ ችለዋል ነው ያሉት፡፡ ሰሜን ጎንደር እና ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች በአካባቢው ከተፈጠረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ምዝገባ ማድረግ አልቻሉም ብለዋል፡፡


መረጃው የአሚኮ ነው።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy