Get Mystery Box with random crypto!

ከትምህርት ተቋማት መረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ድረ-ገጽን መሠረት ያደረገ ዲጂታል መተገበሪያ ተግባራዊ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

ከትምህርት ተቋማት መረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ድረ-ገጽን መሠረት ያደረገ ዲጂታል መተገበሪያ ተግባራዊ ተደረገ

የትምህርት ተቋማት መረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ድረ-ገጽን መሠረት ያደረገ ዲጂታል መተገበሪያ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፤ በአጠቃቀሙ ላይ በተግባር የተደገፈ ሥልጠና መሠጠቱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ስልጠናው የተሰጠው ከመምህራን ኮሌጆች ለተውጣጡና ከመረጃ ጋር ተያያዥነት ላላቸው የትምህርት ባለሙያዎች መሆኑም ተነግሯል።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓትና ኣይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ ሰብስብ ለማ ዲጂታል መተግበሪያው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ከተቋማቱ ጋር በበይነመረብ (በኦንላይን) የሚያገናኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም መረጃዎችን በየፈርጁ እንዲሁም በተቋም ደረጃ እና በአገር አቀፍ ደረጃ በፍጥነት ተንትኖ መረጃው ለሚፈለገው ዓላማ በግብዓትነት እንዲውል የሚያስችልና ለአጠቃቀም ቀላልና ቀልጣፋ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂው ከዚህ በፊት የነበረውን መረጃን በወቅቱና በጥራት ሰብስቦና ተንተኖ ለሚፈልገዉ ግብዓት እንዲውል ማቅረብ ያለመቻል ዉስንነቶችን በሚቀርፍ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የዲጂታል መተግበሪያው ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ ወደ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መረጃ ለሚልኩ ተቋማት በየጊዜው የተላከውን መረጃ ተንትኖ የሚያስቀመጥበት በቂ የማከማቻ ቦታ ያለው መሆኑም ተገልጿል።

በመረጃዎች ላይ ማስተካከያ ካለም ማስተካከያ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነና፤ የተደረገው ማስተካከያንም በቀጥታ በአገር አቀፍ ደረጃ ተንትኖ የሚያስቀምጥ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚዉ መግለጻቸውን አዲስ ማለዳ ከሚኒስቴሩ መሥሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy