Get Mystery Box with random crypto!

በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲያስተምሩ ሊደረግ ነው። በኢትዮጵያ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲያስተምሩ ሊደረግ ነው።

በኢትዮጵያ በቂ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ባለመኖራቸው፣ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሊያስተምሩ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን መምህራንን ጭምር የሚያሠለጥኑ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመድበው የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያስተምሩበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

"የእንግሊዝኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻቸው የሆኑ ሦስት ሺህ የሚሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በአገር ቤት ያሉ መምህራንንና ተማሪዎችን እንዲያስተምሩ በየትምህርት ቤቱ አንድ ለመመደብ አቅደናል" ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ጥሪ መሠረት በውጭ አገር ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውን ወደ አገር ቤት ልከው ትምህርት እንዲሰጡ ለማድረግ እንዲመዘገቡ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት በማድረግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በነፃ የሚያገኝበት ማስተማሪያ ‹‹ፖርታል›› እንደተዘጋጀም ገልጸዋል። #ሪፖርተር
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy