Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ተገድሎ ተገኘ ዛሬ ግንቦት 01/2015 በደብረማርቆስ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ተገድሎ ተገኘ


ዛሬ ግንቦት 01/2015 በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ተገድሎ መገኘቱን እና በዚህም ምክንያት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስጋት መፈጠሩን የተቋሙ ተማሪዎች ነግረውናል።

በጉዳዩ ዙሪያ ለቲክቫህ መረጃ የሰጡት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ድርቧ ደበበ (ዶ/ር)፤ "ፖሊስ ጉዳዩን የያዘው መሆኑንና ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ" ገልጸዋል።

ሟቹ ተማሪ "ቅዳሜ ዕለት የታየ መሆኑን ለሦስት ቀናት ጠፍቶ መቆየቱን" ኃላፊዋ አመልክተዋል።

የተማሪውን ተገድሎ መገኘት ተከትሎ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አለመረጋጋት መፈጠሩንና የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችም ከፀጥታ አካላት ጋር መጠነኛ ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር ከተማሪዎቹ ሰምተናል።አሁን ላይ አለመረጋጋቱ በፀጥታ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።

ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ የተማሪው ማንነትና የግል ማህደር በማጣራት ላይ መሆኑንና በቀጣይ መረጃ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በዚህ ዓመት ብቻ የተቋሙ ተማሪ ተገድሎ ሲገኝ ይህ የመጀመሪያ አለመሆኑንም ተማሪዎቹ ጨምረው ጠቁመዋል
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy