Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ Students News

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students1 — ኢትዮ Students News
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students1 — ኢትዮ Students News
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.96K
የሰርጥ መግለጫ

@bini_business

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-04-04 10:04:53
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል

ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተናገሩት ፦

የመውጫ ፈተና ስትራተጂ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል። ስትራቴጂውን ማስተግበሪያ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል።

ዝርዝር እቅድ ይህ የመውጫ ፈተና እንዴት ? ፤ መቼ ? ፤ በማን ? እንደሚሰጥ ፤ ፈተናው በማን እንደሚዘጋጅ ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሚና የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ምን እንደሚመስል በዝርዝር ምላሽ የሚሰጥ የድርጊት መርሃግብር ተዘጋጅቷል።

የመውጫ ፈተና ሌላ ከውጪ የሚጫን ፈተና አይደለም። በስርአተ ትምህርቱ ውስጥ የተቀመጡትን የምሩቃኑን ፕሮፋይል መሳካት አለመሳካቱን ፤ መጨበጥ አለመጨበጡን የሚያረጋግጥ ነው። "

#ሼር

• ይቀላቀሉን •
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
8.1K views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 23:53:41
Channel recommendation
Sign up to get 5,000 TRX in cash, worth $330, with a 5% daily return on miner purchases.
Official registration link: https://trxcosmos.com/index.html#/register/943678
Wallet usage tutorial: https://t.me/trxcosmos
A TRX cloud mining application from the United Kingdom, introduce friends to register, each person can get 20TRX reward, invite friends or promote investment can also get 10% TRX reward, up to 19%.
Legal White Paper:https://paper.trxcosmos.com/trxserve.pdf
Official website: trxserve.com
Registration event invitation code: 943678
Official customer service telegram: https://t.me/trxserve
Customer Service Manager: @trxserve @trxserve02
Telegram channel: https://t.me/trxcosmos
9.1K views20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 17:50:33
የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ

በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ በ2014 ዓ.ም የሰልጣኞች ቅበላ መቁረጫ ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ዙር እና በሁለተኛው ዙር የ2013 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት ተቀብለው እንደሚያሰለጥኑ ተገልጿል።

Note: የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት ተጠሪነታቸው ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተዛውሯል።

#ሼር

• ይቀላቀሉን •
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
7.8K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 23:46:41
ቀጣዩ የ2014 የዩኒቨርስቲ መግብያ ፈተና ( 12ኛ ክፍል ኢንትራንስ) ተማሪዎች ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል የተማሩትን የትምህርት ይዘት እንደሚያካትት የ ኢትዮ ቲቪ ቻናል የመረጃ ምንጮች ያመላከታሉ

ከትምህርት ሚኒስተር ተጨማሪ መረጃ እየተከታተልን እናሳውቃችኋለን።

#ሼር


• ይቀላቀሉን •
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
8.4K views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 22:23:51 በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላይ ዳግም እርማት እንዲደረግ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ዛሬ ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ የ12ኛ ክፍል መግቢያ ፈተና እና ውጤት ላይ እርማት እንዲደረግ ጠይቋል።

የመግቢያ ፈተናውን ውጤት ተከትሎ የሚወጡት መረጃዎች ያልተለመዱና አስደንጋጭ ናቸው ያለው የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በተወሰኑ ተማሪዎችና ወላጆች ግፊትና ጫና የተስተካከሉ ውጤቶች ለተፈጠረው ስሕተት ኹነኛ ማሳያዎች ናቸው ብሏል።

የአማራ ትምህርት ቢሮ የኹሉንም ትምህርት ቤቶች ውጤት ዝርዝር መረጃ በመሰብሰብ ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚገባው የጠቆመው ፎረሙ ትምህርት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ለችግሩ ትኩረት ሰጥተው ለማረም እድል ያገኛሉ ብሎ እንደሚያምን በደብዳቤው ገልጿል።

በተማሪዎችና ወላጆች እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ሁሉም ወገን በቅንነት ተቀብሎ የድጋሜ እርማትን እንዲሁም ተጨማሪ ማጣራት ማድረግ በዜጎች ዘንድ ፍትሐዊነትና ተዓማኒነት ከማረጋገጡም በላይ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ይጠቅማል ሲልም ፎረሙ አሳስቧል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተናውና ውጤቱ ላይ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች እንደ ፖለቲካ ጥያቄ አቻችሎና ሰምቶ በመተው የሚፈቱ ሳይኾን የትውልዱን እድል የሚወስኑ በመኾናቸው በፍጹም አካዳሚያዊ ሥነ ምግባርና ከፍተኛ መኾን አለበት ብሏል ፎረሙ።

ፎረሙ በጻፈው ደብዳቤም ኹሉም አካላት ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቋል።

ፈተና በደቦ እየተሠራ መልካም ትውልዶችን መፍጠር አይቻልም ያለው ተቋሙ ጉዳዩ ከብሔር አውድ ፍፁም ነጻ እንዲኾን ኹሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲሠሩ ጠይቋል።ተማሪዎችና ወላጆች ጥያቄው መልስ እስኪያገኝ ተረጋግተው እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል።

አሚኮ

• ይቀላቀሉን •
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
8.2K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 09:58:02
በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ነጥብ ላመጣችሁ በሙሉ የዩኒቨርስቲ ምደባ በቅርብ ቀን ጠብቁ

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንድታደርጉ እንጠይቃለን

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን። (ትምህርት ሚኒስቴር)


• ይቀላቀሉን •
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
8.8K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ