Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_real_madrid_14 — ኢትዮ ሪያል ማድሪድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_real_madrid_14 — ኢትዮ ሪያል ማድሪድ
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_real_madrid_14
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 73
የሰርጥ መግለጫ

El Real Madrid Es Mi Corazon ⚪️⚪️
ይህ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ እና ትልቁ የሪያል ማድሪድ የቴሌግራም ቻናል ነው። ስለ ሪያል ማድሪድ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች የዝውውር ዜናዎች ፣ ኃይላይቶች ፣ ቪዲዮች ፣ ትንታኔ በቀጥታ ያገኛሉ !
⚪️HALA MADRID Y NADA MAS⚪️
________________________________
➢ | ለማስታወቂያ ስራ @LeulaRamos

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-10 17:45:40
◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል።  Join
https://t.me/+nn0KRJVHdHVjNGZk https://t.me/+nn0KRJVHdHVjNGZk
9 views Ɯ♬⩔៩ ƙɨ⩎❡ , 14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 17:34:30
ሪያል ማድሪድ በቤንዜማ እና አልቫሮ ሮድሪጌዝ በአጥቂነት ለመቀጠል ወይም በሚቀጥለው የውድድር ዘመን አዲስ አጥቂ ለማስፈረም እስካሁን አልወሰነም።

[#As]

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
572 viewsVᴀɴ Mᴀᴅʀɪᴅɪsᴛᴀs !, edited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 16:44:59
ነገ ከኢስፓኞል ጋር ላለብን ጨዋታ የክለባችን ይፋው ስብስብ

ቤንዜማ ለሊቨርፑሉ ጨዋታ ጥንቃቄ ሲባል በስብስቡ አልተካተተም

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
852 views𝐁𝐥𝐚𝐧𝐜𝐨𝐬, edited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 13:20:49
ናቾ ከቅርብ አመታት በኃላ በሪያል ማድሪድ ቤት ዝቅተኛ ደረጃ ከተሰጣቸው ተጨዋቾች አንዱ ነው። ይህ ስፔናዊ በቡድኑ ውስጥ ቋሚ ተሰላፊ ባይሆንም እድል በተሰጠዉ ጨዋታዎች ላይ ቁርጠኝነቱ እና ብቃቱ አጠያያቂ ሆኖ አያውቅም። ሪያል ማድሪድ በቅርብ ግዜ በደረሰበት የተጨዋቾች ጉዳት ምክንያት ስፔናዊውን ተጨዋች በቡድኑ ውስጥ ያለውን ጠቀሜታ ጎላ አድርጎ አሳይቷል። ምክንያቱም ሁኔታው ​​በሚፈልግበት ጊዜ ናቾ በሁለቱም በግራ እና በቀኝ ተመላላሽነት ላይ ሲያጫዉተዉ ተመልክተናል።

የክሎፕ በአንፊልድ ጥሩ አጀማመር ካደረገ በኋላ ከሊቨርፑል ውድቀት በስተጀርባ ያለውን ብቸኛ ምክንያት ብሎ የሰየመው የናቾ ከፍተኛ ተፅእኖ ነበር። ናቾ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለው ውል በክረምቱ መስኮት ያበቃል እናም በሁለቱ ወገኖች መካከል የኮንትራት ማራዘሚያ ላይ ምንም አይነት ስምምነት የለም። ክለባችን ናቾ እንዲቀጥል ቢፈልግም ተጨዋቹ በብዙ ምክንያቶች ከክለቡ የመልቀቅ ሀሳብ አለዉ።

እንደ SPORT ዘገባ ከሆነ ናቾ ሪያል ማድሪድ ያቀረበለትን የአንድ አመት የኮንትራት እድሳትን ውድቅ አድርጓል። ተጨዋቹ ከክለቡ ጋር ረዘም ያለ ቆይታ ይፈልጋል እናም ቢያንስ ለሁለት የውድድር አመት በክለቡ የሚያየው ፕሮፖዛልን በአፅንኦት ይጠብቃል ተብሏል። የተጨዋቹ ፍላጎት ምክንያታዊ አይደለም ፣ ይሁን እንጂ ከሪያል ማድሪድ ርአዮተ አለም ጋር አይጣጣምም፣ ማድሪድ የአንጋፋ ተጨዋቾችን ኮንትራት ለማራዘም አንድ አመት ብቻ የሚፈቅድ ሲሆን ለዚህም ማሳያ ሰርሂዮ ራሞስ ሲሆን ራሞስ እንኳን በጠረጴዛው ላይ የቀረበውን የአንድ አመት የኮንትራት እድሳት ሀሳብ አልቀበልም በማለት ክለቡን ለመልቀቅ ተገድዷል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 12:17:13
ሰበር

እንሆ Hasta el Final ወይም Until The End የተሰኝዉ የሪያል ማድሪድ ተከታታይ ፊልም ባሁኑ ሰአት የመጀመሪያዉ ክፍል በ Apple TV+ ተለቋል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 12:10:10
ከእሮቡ የባየር ሙኒክ እና ፒኤስጂ የመልሱ ጨዋታ በኋላ የቀድሞ የክለባችን የኃላ ደጀን ሰርሂዮ ራሞስ ብሏል የተባለዉን ንግግር ከከንፈር እንቅስቃሴዉ በመረዳት "የፓሪስን ክለብ የመሰረተው እርጉም ሁን" ሲል ተናግሯል ሲሉ ንግግርን ከፈንፈር እንቅስቃሴ ነጥቀዉ የሚያወጡ ባለሙያዎች ዜናዉን አስፋፍተዉታል።

ነገር ግን ራሞስ ይህንን ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አድርጎታል ምንም እንኳን ኮከቡ መሳደቡን ባይክድም አላማዬ ፒኤስጂ እንዳልሆነ እና የዚህን ክለብ ስም በፍፁም አልጠቀስኩም በማለት ሲናገር ፣ አያይዞም ዜና ከእዉነት የራቀ እና የከንፈር ንባብ ስህተት ነው ብሏል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 11:48:12


@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
1.5K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 11:40:11 ሞድሪች ኮንትራቱን ለማደስ የክለቡን ጥሪ እየጠበቀ ነዉ !

እንደ AS ዘገባ ከሆነ ሉካ ሞድሪች ለሪያል ማድሪድ አንድ ተጨማሪ የውድድር አመት ለማደስ እና በክለቡ ለመጫወት በአካል ብቃት ደረጃ በቂ ሁኔታ ላይ እንደሆነ ይሰማዋል። ክሮኤሺያዊው 37 አመት ቢሆነዉም በከፍተኛ ደረጃ መስራት እንደሚችል በድጋሜ ለክለቡ ማረጋገጥ ይፈልጋል።

ሉካ ለአስር አመታት ያህል የሪያል ማድሪድ የመሀል ሜዳ ዋነኛ ሞተር ሲሆን አሁን ያለው የውድድር አመትም ከዚህ የተለየ አልነበረም። ካርሎ አንቸሎቲ ቡድኑን በተሀድሶ ቢመራውም ልምድ ያለውን ሞድሪችን ግን የቡድኑ የጀርባ አጥንት አካል አድርጎ በማየት ለሁሉም ትልልቅ ጨዋታዎች ቋሚ ተሰላፊ ሲያደርገዉ ተመልክተናል። የ 37 አመቱ ተጨዋች እስካሁን በ 22 የቡድኑ ስኳድ ዉስጥ 24 የላሊጋ ጨዋታዎች ላይ ተጫውቷል ፣ በዚህም 4 ጎሎችን ሲያስቆጥር ሶስት አሲስቶችን አድርጓል። በአንድ ጨዋታ 1.4 ቁልፍ ፓሶችን ሲያደርግ እስካሁን 8 ትላልቅ የግብ እድሎችን ለክለባችን ከፈጠሩ ኮከቦች መካከል አንዱ ነው።

በቅርብ አመታት ክለባችን ሪያል ማድሪድ ለአንጋፋ ተጨዋቾችን ረጅም እድሳት ከመስጠት ተቆጥቧል። እንደሚታወቀዉ ፔሬዝ  ከ 30 አመት በላይ ለሆኑ ተጨዋቾች የአንድ አመት የኮንትራት ማራዘሚያዎችን ማቅረቡ የተለመደ ሲሆን ሆኖም ሞድሪች ያንን ፅንሰ ሀሳብ በቀጣይ ከሚተገበርባቸዉ ተጨዋቾች አንዱ ነው። ሉካ በሳንቲያጎ በርናባው ያለው ኮንትራት በJune ወር ይጠናቀቃል። ሆኖም ሞድሪች አሁን በክለቡ የአንድ አመት የኮንትራት ማራዘሚያ ለመፈረም የተቃረበ ይመስላል ነገር ግን በሚቀጥለው የውድድር አመት የሚጫወተው ሚና በጣም ያነሰ ሊሆን እንደሚችል በብዙዎች ዘንድ ተገምቷል። ሪያል ማድሪድ ጁድ ቤሊንግሀምን በክረምቱ ካስፈረመ ፔሬዝ በቀጣይ የውድድር አመት ክሮሺያዊዉን ኢንተርናሽናልን ቀስ በቀስ ከሜዳ የሚያርቅበትን መንገድ ለመጠቀም ይፈልጋል። ነገር ግን ሞድሪች ሜዳ ላይ ያለዉ ሪከርድ የማያልፍ ከሆነ ካርሊቶ በሁለተኛነት ሚና ማለትም በተቀያሪ ተጨዋችነት ሊያጫዉተዉ ይችላል ተብሏል። [ MARCA ]

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 11:40:02
1.5K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, 08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 10:32:02 ቀጣዩ የአሴንሲዮ መዳረሻ !

ማርኮ አሴንሲዮ ከሪያል ማድሪድ መውጣቱ ባሁኑ ሰአት ክለቡን ከሚለቁ ተጨዋቾች ሰነድ አናት ላይ የተቀመጠ ይመስላል። የ 27 አመቱ ወጣት ክለቡ ያልጠበቀዉን የደሞዝ ጭማሪ ጠይቋል ፣ ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ግንኙነት አፍርሷል ተብሏል።

ይሁን እንጂ የውድድር አመቱ ከጀመረ በኋላ የአሴንሲዮ ሁኔታ ተለውጧል። ከቤንች ወንበር ላይ ተየስቶ ቡድኑ ላይ የሚያሳየዉ ተፅእኖ ለካርሎ አንቸሎቲ ልዩ መሳሪያ ሆኖ ብቅ ብሏል። አሁን ግን ያልታሰቡ ሀሳብን የሚያስለዉጡ ሁኔታዎች ተከስተዋል። የታዳጊዉ አልቫሮ ሮድሪጌዝ የቅርብ ጊዜ ታዋቂነት እየጨመረ በመምጣቱ አሴንሲዮ ላይ ጥላዉን አጥልቷል እናም አሁን ላይ አሴንሲዮ በጣሊያዊዉ ታክቲክ ስር ካሉት የመጨረሻው ምርጫ አጥቂዎች ዉስጥ አንዱ ሆኗል።

እንደ ሙንዶ ዴፖርቲቮ ዘገባ ከሆነ አሴንሲዮ ሪያል ማድሪድ ያቀረበለትን የኮንትራት እድሳት ጥያቄን እስካሁን አልተቀበለም። በቡድኑ ውስጥ የሚጫወተው ሚና በክለቡ የሚቆይ ከሆነ ከተጠባባቂ ወንበር ላይ በመታየት ብቻ እንደሚወሰን ያውቃል ፣ በዚህም ተጨዋቹም ሳንቲያጎ በርናባውን ለቆ ለመውጣት ፈቃደኛ ነው። አዲሱ የአሴንሲዮ ወኪል ጆርጅ ሜንዴስም የደንበኛዉን አገልግሎት ለብዙ የአውሮፓ ክለቦች ይባስ ብሎም ለዋነኛ ባላንጣዉ ተቀናቃኙን ባርሴሎና ጨምሮ አቅርቧል። በእርግጥ ካታላኖች በዚህ የውድድር አመት አሴንሲዮ በርናባዉን የሚለቅ ከሆነ አጥቂውን ለማስፈረም በጣም ጥሩ ቦታ ላይ ከሚገኙት ቡድኖች አንዱ ነው ተብሏል። የ 27 አመቱ ወጣት በዚህ የውድድር አመት 7 የላሊጋ ጨዋታዎችን ጀምሯል። በዚህ ቆይታው አራት ጎሎችን ሲያስቆጥር 3 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። በእያንዳንዱ ጨዋታ 3 ትላልቅ የግብ እድሎችን እና ቁልፍ ቅብብል አድርጓል። ሆኖም በሁለቱም ወገኖች መካከል ስለ አዲስ ስምምነት ንግግሮች አሁንም በመቀጠላቸው ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ካልደረሱ አሴንሲዮ በክረምቱ መስኮት ባርሴሎናን ሊደርስ ይችላል የሚሉ መረጃዎች ተበራክተዋል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk
1.8K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ