Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_real_madrid_14 — ኢትዮ ሪያል ማድሪድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_real_madrid_14 — ኢትዮ ሪያል ማድሪድ
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_real_madrid_14
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 73
የሰርጥ መግለጫ

El Real Madrid Es Mi Corazon ⚪️⚪️
ይህ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ እና ትልቁ የሪያል ማድሪድ የቴሌግራም ቻናል ነው። ስለ ሪያል ማድሪድ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች የዝውውር ዜናዎች ፣ ኃይላይቶች ፣ ቪዲዮች ፣ ትንታኔ በቀጥታ ያገኛሉ !
⚪️HALA MADRID Y NADA MAS⚪️
________________________________
➢ | ለማስታወቂያ ስራ @LeulaRamos

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 243

2022-07-16 08:01:55
ሪያል ማድሪድ ባለፉት ስድስት የውድድር አመታቶች ለተጫዋቾች 567 ሚልየን ዩሮ ወጪ አውጥቷል ። ከተጫዋቾች ሽያጭ ደግሞ 476 ሚልየን ዩሮ ገቢ አስገብቷል ። ይሄ ማለት ሪያል ማድሪድ ባለፉት ስድስት አመታቶች ለተጫዋቾች የተጣራ 91 ሚልየን ዩሮ አውጥቷል እንደማለት ነው ።

በዚህም አውሮፓ ላይ ካሉ ክለቦች ባለፉት ስድስት አመታቶች ለተጫዋቾች ዝውውር ከፍተኛ ገንዘብ ካወጡ ክለቦች በደረጃ 31ኛው ክለብ ለመሆን ችሏል ጀለስ አንብበከዋል ? 31ኛ ነው ያልኩህ እኮ ተገረም እንጂ

በሚገርም ሁኔታ ባለፉት ስድስት የውድድር አመቶች እነዚ ክለቦች በተጫዋቾች ሽያጭ እና ግዢ ከሪያል ማድሪድ በላይ ማውጣት ችለዋል

• ፓርማ 158 ሚልየን ዩሮ ከጣሊያን ዋና ሊግ ከወረደ ሁለት አመት አልፎታል

• አርሰናል 299 ሚልየን ዩሮ
• ሼፊልድ ዩናይትድ 134 ሚልየን ዩሮ ባለፉት ስድስት አመታት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሁለቴ መሳተፍ የቻለ ቡድን
• ብራይተን 259 ሚልየን ዩሮ
• ቶተንሃም 250 ሚልየን ዩሮ
• ፉልሃም 190 ሚልየን ዩሮ አምና በእንግሊዝ ሁለተኛ ሊግ የነበረው
• ላይፕዢግ 176 ሚልየን ዩሮ
• ናፖሊ 165 ሚልየን ዩሮ
• ሌስተር ሲቲ 134 ሚልየን ዩሮ
• ሊድስ ዩናይትድ 115 ሚልየን ዩሮ
• ሃርታ በርሊን 109 ሚልየን ዩሮ በቡንደስሊጋ ላለመውረድ ሚታገል ቡድን
• ዎልፍስበርግ 108 ሚልየን ዩሮ
• ክሪስታል ፓላስ 100 ሚልየን ዩሮ
• ሲቪያ 93 ሚልየን ዩሮ

በሚገርም ሁኔታ እነኚ ሁሉ ቡድኖች ባለፉት ስድስት አመታት በተጫዋቾች ግዢ እና ሽያጭ የተጣራ ያወጡት ወጪ ከታላቁ ሪያል ማድሪድ በላይ ነው ። የፔሬዝ አስተዳደር ከዚም በላይ በጣም በጣም ሊከበር ይገባል

@ETHIO_REAL_MADRID_14
659 viewsAbđįmãdrįdištâ , edited  05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:16:14
ጋዜጣ➛ Jose Felix Duiz (Marca)

ክለባችን ሪያል ማድሪድ ለሴባሎስ እና አሴንሲዮ ማራዘሚያ አይሰጥም እና በዚህ ሲዝን ከቡድኑ ጋር የሚቆዩ ከሆነ አንቸሎቲ ለአንዳንድ ጨዋታዎች በእነሱ ላይ ይተማመናሉ።

ሁሉም በአሜሪካ ውስጥ በግዢ ዙር ውስጥ ይገኛሉ። እና ማንም አይጠፋም።

ዋይኮ መልቀቅ አይፈልግም ነገርግን ባለፈው የውድድር ዘመን ያገኘው ደቂቃዎች የአንዳንድ ቡድኖችን ፍላጎት አነሳስቷል።

ኦድሪያዞላ ከሪያል ማድሪድ ጋር ባለው ኮንትራት ሁለት አመት አለው። እዚህ መቆየት እና ስኬታማ መሆን ይፈልጋል። ይህንን አቋም ለመቀጠል ይለፋል።

ማዮርል ከጌታፌ እና ሴልታ ቪጎ እንዲሁም ከአንዳንድ ቡድኖች ቅናሾች አሉት ብዙ የሚጫወትበት ቦታ መሄድ ይፈልጋል። ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለው ኮንትራት ሊቀረው አንድ የውድድር ዘመን ብቻ ነው።

ማሪያኖ አሁን አቅርቦቱን እያዳመጠ ነው ግን አሁንም ምንም ነገር የለም እና ይሄ ማለት ነው ወደ ሪያል ማድሪድ ኮንትራት ሊቀረው 11 ወር ነው። ማሪያኖ በዚህ ሲዝን ከአንቸሎቲ እቅድ ውጪ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል።

የ ኩቦ ራይንያር ሁኔታ የተለየ ነው። ከፓስፖርት ጋር በተያያዘ በሪያል ማድሪድ ውስጥ ለመቆየት የማይቻል ስለሆነ መፍትሄ መፈለግ አለባቸው።

@Ethio_Real_Madrid_14
@Ethio_Real_Madrid_14
1.5K views𝑎𝑏𝑑𝑢𝑙𝑘𝑒𝑟𝑖𝑚 , 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:09:11
ክለባችን ሪያል ማድሪድ ማክሰኞ July 19 ወደ ሎስ አንጀለስ በመሄድ ከፊቱ ላሉበት ጨዋታዎች ዝግጅቱን ይጀምራል ፥ እናም በ 12 ቀናት ዉስጥ በሶስት የተለያዩ ከተሞች 3 ጨዋታዎችን ያደርጋል።

ቡድናችን በሎስ አንጀለስ ፣ ላስ ቬጋስ ፣ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማዎች ዉስጥ የሚጫወት ሲሆን ከባርሴሎና ፣ ክለብ አሜሪካ እና ዩቬንቱስ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዉን ያደርጋል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:57:48
ሀዛርድ የሚፈልገውን ዝና መልሶ ለማግኘት ከፊቱ ሁለት መሰናክሎች ገጥሞታል እነሱም ቪኒስየስ እና ሮድሪጎ ናቸዉ ሲል MUNDO DEPORTIVO ዘግቧል።

መረጃዉ አያይዞ አንቸሎቲ ለቤልጂየማዊው አዲስ እቅድ አለው እናም ይህ ሀሳብ አዲስ ማእከል መፍጠርን ያካትታል። አዲሱም እቅድ ሀዛርድን ሀሰተኛ 9 ቁጥር ላይ ማጫወት ነው። ዮቪች ከክለቡ ውጪ ሆኗል ፣ አንቸሎቲ ደግሞ በማሪያኖ ላይ እምነት የለዉም። ስለዚህ ሀዛርድን የፈረንሳዩ ተጨዋች ምትክ አድርጎ የማየት እድሉ እየጠነከረ መቷል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14
1.8K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:46:44
በአሜሪካ በሚካሄደዉ ኤል ክላሲኮ አንቸሎቲ ሀዛርድን በአጥቂነት የሚፈትንበት የመጀመሪያ ቀን ሊሆን ይችላል ሲል A.S ዘግቧል።

ካርሊቶ ሉካ ሞድሪችን ሀሰተኛ 9 ቁጥር አጥቂ አድርጎ ከሞከረ በኃላ ሙከራዉ ያልተሳካ በመሆኑ በዚህ ቦታ ላይ ኤዲን ሀዛርድን ከባርሴሎና ጋር ላለብን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊሞክረዉ ይችላል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14
1.7K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:38:16
KPAMG 21 አመት እና ከ 21 አመት በታች ያሉ 10 ምርጥ ተሰጥኦዎችን ያላቸዉን ተጨዋቾች ባወጣው ደረጃ መሰረት ኤድዋርዶ ካማቪንጋ በ £65 ሚሊየን ዩሮ ግምት ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቪኒስየስ ዡኒየር ከኪሊያን ኤምባፔ ፣ ኤርሊንግ ሆላንድ እና ፊል ፎደን በመቀጠል ከ 10 ውድ ተጨዋቾችን ዉስጥ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:26:02
አንደ አዉሮፓዊያኑ ዘመነ አቆጣጠር በ 1989 ልክ በዛሬዋ እለት የክለባችን ተጨዋች የሆነዉ ላውሪ ኩኒንግሀም በማድሪድ ዳርቻ ላይ በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ሞተ ፣ የቀድሞ ተጨዋቻችን በወቅቱ 33 አመቱ ላይ የነበረ ሲሆን ከ 1979 እስከ 1982 የክለባችንን ማሊያ በመልበስ በአጠቃላይ 66 ጨዋታዎችን ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረ ሲሆን 20 ጎሎችን አስቆጥሯል። በተጨማሪም በሪያል ማድሪድ ቤት ቆይታው አንድ ሊግ እና ሁለት የስፔን ዋንጫዎችን አሸንፏል። በጣም ከሚታወሱት ግዜያቱ መካከል በ February 1980 በካምፕ ኑ ያሳየው ድንቅ ብቃት ነበር።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:17:26
1.6K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:13:46
በአሁኑ ሰአት ክለባችን ሪያል ማድሪድ ተጨዋቾችን የመግዛት እቅድ ስለሌለው አንዳንድ ትርፍ ተጨዋቾችን መልቀቅ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

አሴንሲዮ እና ሴባዮስ በኮንትራታቸው የመጨረሻ አመት ላይ ናቸው ፣ ሆኖም ክለባችን የእነዚህን ተጠዋች ኮንትራት ማደስ አይፈልግም። እነዚህ ሁለቱ ተጨዋቾች በገንዘብ ረገድ በጣም አስፈላጊ ሽያጭ ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ነገር ግን ተስማሚ መድረሻ ካላገኙ በዚሁ በክለባችን ይቆያሉ። እርግጥ ነው የክለባችን አስተዳዳሪዎች በኮንትራታቸው የመጨረሻ አመት ላይ የሚገኙት ተጠዋቾች በቡድኑ ውስጥ እንዳይቆዩ ይመርጣሉ።

ቫሌሆ እና ኦድሪዮዞላ ክለቡን መልቀቅ ይችላሉ ፣ ክለቡ በዚህ ላይ ምንም ችግር የለበትም። ሁለቱም በአዲሱ የውድድር አመት ሜዳ ላይ ጥቂት የመጫወቻ ደቂቃዎች እንደሚኖራቸው ከወዲሁ ያውቃሉ። ማዮራል ከሴልታ ቪጎ እና ሄታፌ ጥያቄዎች ቀርበዉለታል ፣ ስለዚህ ተጨማሪ የመጫወቻ ደቂቃዎችን ለማግኘት ሊሄድ ይችላል። ምንም እንኳን ማሪያኖ ወደተለያዩ ክለቦች ይሄዳል በሚሌ የተለያዩ ጥቆማዎች ቢሰሙም ስለሱ እስካሁን ምንም አይነት ዜና የለም ፣ ኩቦ ደግሞ ካርሎ በእሱ ላይ እንደማይተማመን ጠንቅቆ ያዉቃል። ስለዚህ ኩቦ እና ሬኒየር ክለባችንን ከመልቀቅ ሌላ ምንም አማራጭ የላቸውም ምክንያቱም በሪያል ማድሪድ ቤት አውሮፓውያን ያልሆኑ ተጨዋቾች ከተሰጣቸዉ ቦታ በዝተዉ ሰለሚገኙ።

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14
1.7K viewsʟᴇᴜʟᴀ ʀᴀᴍᴏs, edited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 20:30:20
#መረጃ ➛ Relevo

ኢስኮ ወደ ሲቪያ ሊዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።

@Ethio_Real_Madrid_14
@Ethio_Real_Madrid_14
1.7K views𝑎𝑏𝑑𝑢𝑙𝑘𝑒𝑟𝑖𝑚 , 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ