Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_news1 — ETHIO NEWS E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_news1 — ETHIO NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_news1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.01K
የሰርጥ መግለጫ

✍ በየእለቱ ትኩስ እና አዳዲስ የሀገር ውስጥ የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ
ለእውነተኛ ለትክክለኛ መረጃ ብቻ እንሰራለን። ✍

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-13 17:30:12
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ መደረጉን አስታወቀ፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሀምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ለሚዲያ በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የተለያዪ የማጭበርበር ድርጊት ግኝቶች ስለተገኙበት ውድቅ መደረጉን የገለፁ ሲሆን በቅርቡ ዕጣው በድጋሜ እንዲወጣ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡

ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንቀርባለን።

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777
1.2K views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:06:52 1997 ነባር 20/80 ባለ አንድ መኝታ ዝርዝር ተለቀቀ።
https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777
1.7K views10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:25:00
3.3K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:32:57 እጣ የሚወጣበት ቀን ለአርብ ሐምሌ 1/2014 ተቀይሯል
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ ሊያስተላለፍ ነው፡፡ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከ2006/07 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታቸው ሲካሄዱ የቆዩ በ40/60 ለ3ኛ ጊዜ እና በ20/80 14ኛ ጊዜ በድምሩ 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

በመግለጫው ላይ ከተማ አስተዳደሩ የተረከባቸውን 139 ሺህ ቤቶች ውስጥ 96ሺህ ያህል ቤቶች በእጣ፤ በውሳኔ እና በምደባ የተሰጡ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ እጣ 25ሺ 491 ቤቶች እጣ እንደሚወጣባቸው አስታውቀዋል፡፡

በተለያየ መንገድ ከተላለፉትም 96ሺህ ቤቶች ውስጥ 54 ሺህ ያህሉ ቁልፍ መረከባቸው የተገለፀ ሲሆን ሌሎችም ቁልፍ ያልወሰዱ ቁልፋቸውን እንዲረከቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በ14ኛው ዙር እጣ ብቁ የሚሆኑትን ተመዝጋቢዎች በተመለከተ የ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም ድረስ የቆጠቡና እና የ40/60 40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም እንደሚሆኑ ተገልጧል፡፡

በዚህም መሰረት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

በዚህ ዙር ከሚተላለፉ ቤቶች ውስጥ ከዚህ በፊት በማጣራት ሂደት የተገኙ ቤቶች ለልማት ተነሺ ሲስተናገዱበት ቆይተው የቀሩት እንዲካተቱ መደረጉን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ባለፉት የቤት ልማት ፕሮግራም ከጀመረበት አንስቶ በ17 ዓመታት ውስጥ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተቻለው 300 ሺህ ያህል ቤቶችን ብቻ መሆኑን ገልፀው ፤አሁንም በሚወጡት ውስን ቁጥር ያላቸው ቤቶች የህብረተሰቡን ችግር መቅረፍ ስለማይችሉ ፤ከተማ አስተዳደሩ አምስት አይነት የቤት ልማት አማራጮችን መዘርጋቱን አስታውቀዋል፡፡

ከነዚህም መሃከል
በመኖርያ ህብረት ስራ ማህበር ፤12ሺህ ያህል ሰዎች ከነበሩት ተመዝጋቢዎች ውስጥ አሁን ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
በመንግስትና በግል ባለሀብቶች አጋርነት /public private partnership/ በ70/30 የግንኙነት ስርዓት
በመኖርያ ቤት በሽርክና ማቅረብ/Joint Venture /፣

የግል አልሚዎች በማበረታታት የህብረተሰቡን የቤት ችግር ለመፍታት አስተዳደሩ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የቁጠባ ቤቶችን መገንባት በተመጣጣኝ ኪራይ ማቅረብም አማራጭ
እንደ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አገላለፅ ‹‹ይህ አመራር የተረከባቸው ቤቶች በአጠቃላይ በርካታ ተግዳሮቶች የነበሩባቸው ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ፤የማስተላለፍያ፤ የመሠረተ ልማት አቅርቦት ችግር ፤ የቤቶቹን ግንባታ ጥለው የጠፉ ኮንትራክተሮች ፤ የብድር አቅርቦት እግር እንዲሁም የዋጋ ንረት የመሳሰሉት ተግዳሮቶችን መጋፈጡን አስታውሰዋል፡፡

ነገር ግን እነዚህ እክሎች በማለፍ በአጠቃላይ አስተዳደሩ ከባንክ ቦንድ ብድር ብር 18.7 ቢሊዮን እና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ከመደበኛ በጀት ብር 2.871 ቢሊዮን በድምሩ ብር 21.571 ቢሊዮን መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የአንድ ካሬ ማስተላለፊያ ዋጋን በተመለከተም 20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም 7,997.17 ብር 40/60 ቤት ልማት ፕሮግራም 11,162.97 ብር ሲሆን በግል አልሚዎች ከሚሰሩ ተመሳሳይ ቤቶች አኳያ ይህ የአንድ ካሬ ማስተላፊያ ዋጋ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ቀርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘር ያስሚን ዋህብረቢ በበኩላቸው ቤቶቹ 97 በመቶ አማካኝ አፈፃፀም ላይ የደረሱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሁን የምንጠቀምበት የእጣ አወጣጥ ሶፍትዌር በተመለከተ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ) ያበለፀገውና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የፌደራልንም ጨምሮ ታይቶ ይሁንታን ያገኘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመበልጸግ ሂደት ብዙ ሙከራዎች የተካደለት ቅድመ-ዝግጅት ለአራት ዙር ሙከራ ተደርጎበት፣ አምስተኛውና የመጨረሻ ዙር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከታዛቢዎች ተገኝቶ እንደሚሞከር ተገልፅዋል፡፡

ሲስተሙ ተጠያቂነትን ማስፈን የሚችል ኦዲት መደረግ የሚችል መሆኑ ገልፀዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ታምራት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የቤት አወጣጡ እንደ ቅደም ተከተል ቅድሚያ የ97 ተመዝጋቢዎች እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የቤት ዓይነትና ብዛት በተመለከተ
የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም
አያት 2፤ ቦሌ በሻሌ፤ ቡልቡላ ሎት 2 ሲሆኑ
የ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም
በረከት፤ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፤5፤6)፤ ወታደር፤የካ ጣፎ፤ ጀሞ ጋራ፤ ጎሮ ስላሴ፤ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል ናቸው፡፡
በዚህ አጋጣሚ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተጀመሩት የተገጣጣሚ ቤቶች የነበረባቸው የፍርድ ቤት እግድ ተነስቶ በፍጥነት እየተገነባ መሆኑ ተገልጧል፡፡


https://t.me/Ethio_news1
https://t.me/Ethio_news1
8.7K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:00:49
#የ40_60_መረጃ

1. ጠቅላላ የተሰሩ ቤቶች
ድምር = 38,790

2. ጠቅላላ የተሰሩ የመኖሪያ ቤቶች
ብዛት =30,076

3. ጠቅላላ የተሰሩ የንግድ ቤቶች
ብዛት =8,714

4. በ1ኛና 2ኛ ዙሮች ጠቅላላ እጣ የወጣባቸው የመኖሪያ ቤቶች
ብዛት =19,366

5. ጠቅላላ እጣ ያልወጣባቸው የመኖሪያ ቤቶች
ብዛት =10,710 (ላለፉት አመታት ካለ እጣ የተላለፉ የ40/60 ቤቶች ከዚህ የቤት ቁጥር ላይ የሚቀነስ ይሆናል)

https://t.me/Ethio_news1
https://t.me/Ethio_news1
2.2K viewsedited  12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 12:16:34
በመዲናዋ የ40/60 እና የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ነገ ይካሄዳል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ከተማ አስተዳደሩ በነገው ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበው ለሚጠባበቁ የህብረተሰብ ከፍሎች 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ተኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት እንደሚያካሂድ ተመላክቷል፡፡

የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሚመለከታቸው የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችና ታዛቢዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://t.me/Ethio_news1
https://t.me/Ethio_news1
2.6K viewsedited  09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:31:33
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደረገ
*****

ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ መሠረት፦

ቤንዚን …. 47 ብር ከ83 ሣንቲም በሊትር
ነጭ ናፍጣ …. 49 ብር ከ02 ሣንቲም በሊትር
ኬሮሲን… 49 ብር ከ02 ሣንቲም በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ … 53 ብር ከ10 ሣንቲም በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ … 52 ብር ከ37 ሣንቲም በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ … 98 ብር ከ83 ሣንቲም በሊትር መሆኑን አስታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ እና የትርፍ ህዳግ አሠራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

https://t.me/Ethio_news1
https://t.me/Ethio_news1
9.9K viewsedited  17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 21:15:32
ከነገ ሚያዚያ 30 ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

ከታኅሣሥ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ወራት ቤኒዝኒን በሊትር 31 ብር ከ74 ሳንቲም፣ ናፍጣ ደግሞ በሊትር 28 ብር ከ98 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኖ ነበር።

በሚያዚያ ወር በዓለም ገበያ ነዳጅ የተገዛበት መሸጫ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ ቀጥታ ተሰልቶ ተግባር ላይ ቢውል በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ሊትር ናፍጣ መሸጫው 73 ብር እንደዚሁም የአንድ ሊትር ቤንዚን መሸጫ ዋጋ 66 ብር ከ78 ሳንቲም ይሆን ነበርም ብሏል።

ሆኖም ሀገሪቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከዓለም መሸጫ ዋጋ ልዩነትን 85 በመቶ የሚሆነውን ጫና መንግሥት በመሸከም ቀሪውን 15 በመቶ ለተጠቃሚው እንዲተላለፍ በመወሰን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት

#ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ፣
#ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
#ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
#ቀላል_ጥቁር_ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣
#ከባድ_ጥቁር_ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም
#የአውሮፕላን_ነዳጅ በሊትር 78 ብር ከ87 ሳንቲም እንዲሆን መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

https://t.me/Ethio_news1
https://t.me/Ethio_news1
6.8K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 08:47:19
ሰበር ዜና!!

የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR6600/S3199 ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ እንዲቋረጥ ወሰነ።

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777
7.7K views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 20:51:19
ሰበር ዜና
የብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ
**********************

የብልግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በ1486 ድምፅ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ፡፡

በተጨማሪም ጉባኤው አቶ አደም ፋራህን በ1370 ድምፅ እንዲሁም አቶ ደመቀ መኮንንን በ970 ድምፅ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አድርጎ መርጧቸዋል፡፡
10.2K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ