Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_news1 — ETHIO NEWS E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_news1 — ETHIO NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_news1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.01K
የሰርጥ መግለጫ

✍ በየእለቱ ትኩስ እና አዳዲስ የሀገር ውስጥ የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ
ለእውነተኛ ለትክክለኛ መረጃ ብቻ እንሰራለን። ✍

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-28 18:07:41
የተወዳጁና ድምጸ መረዋው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ሐሙስ መስከረም 19 ቀን 2015 በአዲስ አበባ አራት ኪሎ መንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን እንደሚፈጸም የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው አስታወቀ።

የተወዳጁን የኪነጥበብ ሰው ሥርዓተ ቀብር ለማስፈጸም የተቋቋመው ኮሚቴ ጉዳዩን አስመልክቶ በአርቲስቱ በመኖሪያ ቤት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

አርቲስት አረጋኸኝ ወራሽ፥ የወንድማችን ህልፈት ድንገተኛ በመሆኑ ሀዘናችን መሪር ነው፥ በዚህ ሁኔታ መግለጫ መስጠትም ከባድ ነው ብሏል።

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅን በአጭር መግለጽ ከባድ ነው፤ በህይወት ዘመኑ የሰራቸው ተግባራት ግን ትውልድ የሚማርባቸው ይሆናሉ ሲል ገልጿል።

በነገው ዕለት የአስከሬን ስንብት በመኖሪያ ቤቱ በማድረግ በወዳጅነት ፓርክም ከ6፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በመንግስት ኃላፊዎች፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ የአስክሬን ስንብት እንደሚካሄድ ገልጿል።

በመቀጠልም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም ተናግሯል።

ጎልማሳው የጥበብ ሰው ማዲንጎ አፈወርቅ ስለ ፍቅር፣ ትዝታ፣ ባህል፣ ሀገር፣ ታሪክና ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ መልዕክቶችን በተስረቅራቂ ድምጹ በማዜም በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ስራ ላይ የራሱን አሻራ አሳርፏል።

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሄድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት መሆኑም ይታወቃል።

በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሀገር አዘዞ ተወልዶ በደብረታቦር ያደገው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ መስከረም 17/2015 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
452 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 16:39:28
አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*******************

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው አርቲስቱ ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ሕክምና ማድረጉንና ከቆይታ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም ለተጨማሪ ምርመራ አስከሬኑ ወደ ሆስፒታል መላኩንም ለማወቅ ተችሏል።
907 views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 14:18:46

1.1K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 11:41:23 https://www.facebook.com/107429748752514/posts/pfbid02zCGoJwVhhpGVSHsKoJavDxAyHVyR354DZAbRw2bWEVaoxcgiLwsVDs7M7EBxQkMil/
1.8K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 08:23:34 https://www.tiktok.com/t/ZTRa6VFxT/
2.0K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 05:35:23
"ሞኝን እባብ ሁለቴ ነክሰው! ሳያይ እና ሲያሳይ" እንዲሉ...
ህወሓት ዛሬ ያወጣው መግለጫ መጋቢት 2014 አውጥቶት ከነበረው ጋር አንድና ተመሣሣይ ነው
3.7K views02:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 08:07:41 ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ!
       
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር  ከነሐሴ 26/ 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም  ባለው ጊዜ ውስጥ  መስፈርቱን የሚያሟሉ  ወጣቶችን መልምሎ በመደበኛ ሰራዊትና በእጩ መኮነንነት በማሰልጠን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ማድርግ ይፈልጋል ፤

የመመልመያ መስፈርቶች ፦

1. ህገ- መንግስቱን የተቀበለ/ች ለዚህ በፅናት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች

2. በብሔር-ብሔረሰቦችን እኩልነት የሚያምን /የምታምን

3. ከአሁን በፊት የፖሊስ ወይም የመከላከያ አባል ያልነበረ/ች

4. ከወንጀል ነፃ የሆነ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ክርክር የሌለበት/ባት

5. ከማንኛውም ሱስና አጉል ልማድ የፀዳ/ች እና ሙሉ ጤንነት ያለው/ያላት

6. በመከላከያ ለ7 ዓመት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች በማንኛውም ቦታ ተመድቦ መስራት የሚችል/የምትችል

7. ፆታ፡- አይለይም

8. ኢትዮጵያዊ የሆነ/ች በሚኖርበት ቀበሌ 2 ዓመት የኖረ/ች

9. ዕድሜ፡- ከ18-25 አመት ፤ ቁመት ለወንድ 1.60 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴት ደግሞ 1.55 እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች

10. ክብደት፡-ለወንድ ከ50-75 ኪ.ግ የሆነ ለሴት ደግሞ 45-66 ኪሎግራም የሆነች፣

11. የትምህርት ማስረጃ፦ ለወንድ 6ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና ለሴት እወቅና ካለው የትምህርት ተቋም ዲፕሎማ ወይም በሌቭል ያጠናቀቁ እና ከዚያ በላይ የሆኑ የ 8ኛ ክፍል የሚኒስቲሪ ካርድ ማቅርብ የሚችሉ ፣

12. ያላገባ/ችና ያልወለደ/ች

13. ደመወዝ በመከላከያ ስኬል መሰረት ሆኖ ጥቅማጥቅም የመኖሪያ ቤትና ህክምና አገልግሎት በነፃ የሚያገኙ  ሲሆን በመከላከያ ዕቅድና ፍላጎት መሰረት በትምህርት ተቋም ገብተው የመማር ዕድል አላቸው፣

14. የምዝገባ ቦታ ፦ በሁሉም የክልል ከተሞች የፀጥታ ተቋማት ቢሮ( ሚሊሻ ፤ ፖሊስ ፤ ሰላምና ደህንነት ቢሮዎች )

15. የምዝገባ ቀን፡-  ከነሐሴ 26/2014 ዓ/ም ጀምሮ   አስከ መስከረም 10/2015 ዓ/ም  ዘወትር በሥራ ስዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ

ማሳሰቢያ፡- በምዝገባ ወቅት መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች የቀበሌና የፖሊስ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የትምህርት ማስረጃ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የቀበሌ መታወቂያ በዘመኑ የታደሰ ያስፈልጋል።

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777
577 views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:37:38
የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

https://t.me/Ethio_news1
https://t.me/Ethio_news1
974 viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 10:59:18
የኡሁሩ ልጆች ሦስተኛ ላይ መጥተው አድፍጠዋል። ቀጣይ ውድድሮች ለሁለቱ ሀገራት ወሳኝ ናቸው ። ድል ለኢትዮጵያ!!
4.2K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:44:37
የሴቶች ማራቶን ወርቅ: #ኢትዮጵያ!
እንኳን ደስ ያለን!

አትሌት ጎይትቶም ገ/ስላሴ የዮጁን ማራቶን አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ ወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች!
5.0K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ