Get Mystery Box with random crypto!

የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነገ ከሰዓት ላይ የሚካሄደው የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓ | ETHIO NEWS

የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነገ ከሰዓት ላይ የሚካሄደው የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱም በቴሌቪዠን #በቀጥታ_ስርጭት ይተላለፋል።

** 25 ሺህ 791 የ40/60 እና 20/80 ቤቶች ዕጣ ይወጣባቸዋል።

** በእጣ 146 ሺህ 892 እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በቂ ቁጠባ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ።

** ነባርና በ2005 ዓ.ም በባለ 3 መኝታ ቤት የተሰሩ 300 ቤቶችም ይተላለፋሉ

** በእጣው ብቁ የሚሆኑት የ20/80 (ስቱዲዮ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን የ84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ መሆን ይገባቸዋል

** የ40/60 ተመዝጋቢዎች ከ40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው ለእጣ ውድድር ብቁ የሆኑ እስከ የካቲት 21/2014 ዓ.ም ድረስ መሰረት 40% የቆጠቡ።

** በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 93,352 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 53,540 በአጠቃላይ 146,892 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው በዚህ ዙር ዕጣ ተካትው የቤት እድለኛ ለመሆን የሚወዳደሩ ይሆናል።

https://t.me/Ethio_news1
https://t.me/Ethio_news1