Get Mystery Box with random crypto!

#Peace ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ? የፕሪቶሪያ ስምምነትና የዛሬው ናይሮቢ ስምምነ | ETHIO NEWS

#Peace

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?

የፕሪቶሪያ ስምምነትና የዛሬው ናይሮቢ ስምምነት ተፈፃሚ እንዲሆን ለማድረግ በሙሉ ቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

ጀነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

የዛሬው ስምምነት በትግራይ ውስጥ በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ያስወግዳል የሚል ተስፋ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

ኡሁሩ ኬንያታ ምን አሉ ?

ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው መግለጫ ስምምነቱ በጦር ወንጀሎች ላይ " ተጠያቂነትን " ያጠቃልል እንደሆነ ለተጠየቀ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተው ነበር።

ኡሁሩ ኬንያታ ይህ " የመሳሪያ ድምፅ ፀጥ ሲል እና አስከፊው የሰብአዊ ሁኔታ ሲስተካከል " እንደሚመጣ ተናግረዋል።

" በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግፍ የሚፈጽም አካል ላይ ከባድ ማዕቀብ ይጣልበታል " ብለዋል።