Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Neshida & Menzuma

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_neshida
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.99K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ #YouTube ቻናል 👇
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma
ወደ #Facebook Page 👇
https://www.facebook.com/Ethio-Neshida-Menzuma-348031129044029/
ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት(bot) ተጠቅሞ ያድርሱን✍️
👇
@ETHIO_NESHIDA_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-10-07 03:21:09
اللهم صل وسلم على سيدنا محمد!
850 viewsedited  00:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 23:42:21 ይጣራል ያ ነቢ ብሎ
አንቱን ለማየት ከጅሎ

https://vm.tiktok.com/ZMFYBsRp1/
363 viewsedited  20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 23:03:35

510 views20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 21:52:37 #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

#ሙሐመድዬ_የከውኑ_ጀምበር!

በሐዲስ ሸሪፍ ላይ "የትንሳኤ እለት ከእኔ ቅርብ የሚቀመጠው በእኔ ላይ ሶለዋት ያበዛ ሰው ነው።" ብለዋልና የሸፊዕህን ሥም እየከረርክ ተከተለኝማ!

በክዋኔ ፍጥረታት ውስጥ ታላቁ ክስተት የቂያማ (ትንሳኤ) ቀን ነው። ይህ እለት እውነት ከሀሰት የሚለይበት ነው። በዚህ ቀን ውሸት ተወግዶ ሀቅ ይነግሳል። "ትንሳኤ" የተከሰተች እለት እንዲህ ያለ ክስተት ይከሰታል………
መላኢካው ሰይዱና ኢስራኢል ጡሩንባውን ይነፉታል። ይህ ጡሩንባ በእያንዳንዱ ፍጡር ልክ አፍ አለው። ከአንድ ቀዳዳ በኩል የተነፋው ድምፅ ለሁሉም በየስሙ በኩል ባለው ቀዳዳ ይሰማዋል። ሁሉም አፈር ከሆነበት ይቀሰቀሳል። ወዲያውኑ ወደ "ፍርድ" ሜዳ ይነዳሉ። ፍጥረት የተባለ ሁሉ ጌታው ፊት ይቀርባል። የ "ተውሒድ" ባለቤቶች በዚያን እለት አስታራቂ ፍለጋ ይንከራተታሉ። አባታቸው አደም ጋር ይሄዳሉ ፣ ሆኖም ምልጃ ሳያገኙ ይቀራሉ። ቀጥለውም ወደ ኑህ እንዲህ እንዲህ እያሉ ወደ ሰይዱና ሙሐመድ (ዓለይሂ ሶላቱሏሂ መዓ ሰላሚሂ) ይሄዳሉ። ነብዩና ሙሐመድም (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) "ለዚህች እለት እኔ አለሁላት" ይሏቸዋል።

ወዲያውኑ በዓርሽ ስር በአንገታቸው ድፍት ብለው ይወድቃሉ ፣ ግንባራቸው መሬትን ለሱጁድ ትታከካለች። አንድ ሰው በዝናብ የሚበሰብሰውን ያህል እርሳቸውም በጌታቸው "ኑር" ተነክረው እስኪርሱ ድረስ አንገታቸውን ቀና ሳያደርጉ ይቆያሉ። ከጌታቸው ጋር የሚጣፍጥ ወግ እስኪነጋገሩ ድረስ በሱጁዳቸው ይቀጥላሉ። ከምልጃ የተመኙትን ያህል እስኪያገኙ ግንባራቸውን በመሬት ያቆያሉ። ይህን ጊዜም ጌትዬ "ቀና በል፣ ተናገር ትሰማለህ ፣ ጠይቅ ትሰጣለህ ፣ አማልድ ትማለዳለህ" ብሎ ያባብላቸዋል። ሸፈዓ የማይቀር ክስተት ነው። ገና በአዘል ለነብዩ የተደገሰላቸው ነው። ለዚህም ነው አሏህ በረቀቀው ንግግሩ በሱረት‐ተውባ የመጨረሻ አናቅፅት ላይ "عزيز عليه ما عنتم" የሚለን። "እናንተ ለእርሱ ገና አልተፈቀደም የምትሉት ሸፈዓ ለእርሱ ተፈቅዷል ፣ ግዴታ ተደርጋለታለችም" በማለት የራቀውን ምስጢር ዓሪፎቹ አቅርበው አስተምረውናል።

ይህ ክስተት የሐቢበሏህን (ዓለይሂ ሰላም) ልቅና የሚያመለክት ነው። "ሸፈዓ" በማድረግ ያላቸውን ደረጃ ያሳያሉ። በ"መቃመል‐መሕሙድ" ይነግሳሉ። "ወሲላ" እና "ፈዲላ" ላይ ይደላደላሉ። በቂያማ እለት ሰዎች ከሚያከብሩት ትልቁ መውሊድ አንዱ የሸፈዓ ጊዜ ነው። በነብዩ መደሰት በዚያኛውም ዓለም ይዘልቃል። በዚያ እለት ከሚደሰቱት ያድርገን!

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
Atiqa Ahmed Ali
916 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 21:52:32
811 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 21:28:58 https://www.tiktok.com/@ethioneshidamenzuma/video/7151467292788788486?_r=1&u_code=dc2hc63a55mkcd&preview_pb=0&language=en&_d=dk50d1k16e2l3a&share_item_id=7151467292788788486&source=h5_m×tamp=1665080920&user_id=6818080163991323654&sec_user_id=MS4wLjABAAAAhLtNTqVXsetRatV3_AUrn3bEYETGX2AcpgeKwBykobzGE8cxUR0gCzgnXcPpChU4&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7146959023694202630&share_link_id=5cbd9815-b3aa-49f4-97bc-e8a3fb35d59b&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main
947 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 19:07:00 Fuad Shemsu ሀያተል አለም ተለቀቀ



1.4K viewsedited  16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 21:42:42 #ሙሐመድዬ_የከውኑ_ጀምበር!

እንኳን ሠው ደመናም ኻዲማቸው ነበር። ባለፉ ባገደሙበት ሁሉ እየተዟዟረ ያጠላላቸዋል።

ሶሐብዩ ሠይድ ዐብዱሏህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሐቢበሏህን ﷺ ጫማና መፋቂያ ያዥ ነበሩ። ጫማቸውን ያደርጉላቸዋል። በዬሄዱበትም ዱላቸውን ይዘው ይከተሏቸዋል። የሚቀመጡበት ቦታ ሲደርሱ ጫማቸውን ያወልቁላቸውና እጃቸው ላይ ያንጠለጥሉታል ዱላቸውንም ያቀብሏቸዋል። ሐጃቸውን ጨርሰው ሲቆሙ ጫማቸውን ያደርጉላቸውና ፊት ለፊታቸው እየሄዱ ከሳቸው ቀድመው ቤታቸው ይገባሉ።

የትልቁ ሠው ኻዲም መሆን ምንኛ መታደል ነው። አርሽን የረገጠውን ጫማ ልክ እንደ ጌጥ ክንዳቸው ላይ አንጠልጥለውት በደስታ ይጠብቁ ነበር።

አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
Atiqa Ahmed Ali
856 viewsedited  18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ