Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ጀምሬ ይሰጣል። የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ | ኢትዮ መረጃ University

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ጀምሬ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም። ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።