Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የትምህርት ሚኒስቴር ' የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ ' ን በማጸደቅ | ኢትዮ መረጃ University

#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር " የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ " ን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሰራጭቷል።

በ2015 የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚሆነው መመሪያው፤ የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ ነው ተብሏል።

መመሪያ ቁጥር 919/2014 ሆኖ በፍትህ ሚኒስቴር የጸደቀውን መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ መሰራጨቱ ታውቋል።

አምስት ክፍሎች እና 27 አንቀጾች ያሉት አዲሱ መመሪያ፤ ከነሐሴ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና እንደሆነ ተደንግጓል።

በመመሪያው ላይ የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በማንኛውም ሁኔታ የጣሰ፣ እንዲጣስ ያደረገ በማንኛውም ደረጃ ላይ ያለ አስፈጻሚና ፈጻሚ አካል ተጠያቂ እንደሚሆን በመመሪያው ተመላክቷል።