Get Mystery Box with random crypto!

#Update ከ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጋር ተያይዞ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ማቅረብ እን | ኢትዮ መረጃ University

#Update

ከ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጋር ተያይዞ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ተማሪዎች ቅሬታቸውን ወደ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በአካል በመሄድ ማቅረብ እንደሚችሉ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበበ ቸርነት ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ ውጤት ወደየትምህርት ቤቶች መላኩን የገለጹት ኃላፊው፤ በተፈጠረው የኔትወርክ መጨናነቅ ምክንያት ውጤታቸውን ማየት ያልቻሉ ተማሪዎች ወደትምህርት ቤታቸው በመሄድ ማየት እና መውሰድ ይችላሉ ብለዋል፡፡