" የተቀመጠው አድራሻ በአግባቡ ስለማይሰራ ውጤታችንን ማየት አልቻልንም " - ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘንድሮው የስምንተኛ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።
ቢሮው ተማሪዎች ውጤታቸውን https://aaceb.gov.et/%e1%8b%a88%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8b%89%e1%8c%a4%e1%89%b5/ ወይም aaceb.gov.et ላይ በመግባት ማየት እንደሚችሉ ገልጾ ነበር።
ነገር ግን ቢሮው ይፋ ያደረገው ውጤት መመልከቻ አድራሻ በትክክል ስለማይሰራ ውጤት ለማየት እንዳልቻሉ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች አሳውቀዋል።
በመሆኑም ፤ የከተማው ትምህርት ቢሮ አድራሻው ላይ ያለውን ችግር እንዲያርም /እንዲያስተካክል እንዲሁም ለህዝብ ይፋ ከመደረጉ በፊት ተገቢውን ፍተሻ ማለፉን ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 29 /2014 ዓ/ም በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይፋ በተደረገው መረጃ ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፤ 85.5% ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል ለመዛወር ችለዋል።