Get Mystery Box with random crypto!

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ጠዋት በኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ጠዋት በኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል በመገኘት በእሣት ቃጠሎ የተጎዱ ነዋሪዎችን አነጋገሩ

በትላንትናው እለት በኮልፌና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ መነሻ በማጣራት እርምጃ እንደሚወሠድና በቃጠሎው ለተጎዱ ነዋሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ጠዋት በኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል በመገኘት በእሣት ቃጠሎ የተጎዱ ነዋሪዎችን ለማፅናናትና የደረሠውን ጉዳት በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል።

በሁለቱም አካባቢ የተነሣው እሣት ድንገተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሠባቸው ነዋሪዎች መፅናናት እንዳለባቸው ገልፀው የከተማ አስተዳድሩ አስፈላጊው ሁሉ ለማድረግ ከጎናቸው እንደሚቆም ወ/ሮ አዳነች
ገልፀዋል።

በአደጋው የተቃጠሉ የሱቆች እና የቤቶች ብዛት ፣ በጠቅላላው የደረሰውን ጉዳት በፖሊስ እየተጣራ ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች ፤ የእሳት ቃጠሎው መነሻ ለማወቅ በሚደረገው ጥረት እና ለጋራ ሰላማችን ሲባል ምንም አይነት መረጃ ያለው ሰው ለህግ አስከባሪ እና ለፖሊስ መረጃውን በመስጠት እንዲተባበር መጠየቃቸውን የከተማ አስተዳሩ መረጃ ያሳያል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news