Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እንዲያሳውቅ ተጠየቀ። ትምህርት | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እንዲያሳውቅ ተጠየቀ።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን 'ቁርጥ' ያለ ቀን እንዲያሳውቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በበኩላቸው "ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ለማሳወቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ 'ታብሌቶች' ወደ አገር ውስጥ አልገቡም" ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እንደሚሰራና 'ታብሌቶቹ' ወደ አገር ሲገቡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደሚወሰን ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በ1 ሺህ 500 የፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል። (ENA)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news