Get Mystery Box with random crypto!

#Tigray! የሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ ከመከላከያ ሚኒስ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

#Tigray!

የሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ ከመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ጥሩዬ አሰፌ ጋር ትላንት ጥር 22 ቀን 2013 ምክክር ማድረጋቸው ተሰምቷል።

በወቅቱ በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ "ፆታዊ ጥቃቶች" ተፈፅሟል በሚል የተነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት እንዳደረጉ ነው የተገለፀው።

ጉዳዮን ለማጠራት የተቋቋመውን ግብረ ሀይል አስመልክቶ ውይይት የተደረገ ሲሆን ግብረ ሀይሉ የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግን እና መከላከያ ሰራዊትን ያካተተ መሆኑ ነው የተሰማው።

ግብረ ሀይሉም እውነተኛው ነገር ለማወቅ ምርመራ እና የማረጋገጥ ስራ እንደሚያከናውን ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ገልፀዋል።

መረጃው የሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news