Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት በድምፂ ወያነ ትግራይ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለህዝቡ መልዕክት አስተላለፉ!

ዶ/ር ደብረፅዮን በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት አስመልክቶ "ህዝቡ ራሱን በራሱን የማስተዳደር መብቱን በተግባር ለማረጋገጥ በፅናት ስለታገለ የተቃጣበት ጦርነት" ያሉት ሲሆን አራት መንግሥታትና የክልሎች ልዩ ኃይሎች ተሳትፈውበታል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ያለው ትግል እንደቀጠለና በክልሉ ከነበረው ሰሜን እዝ የተገኘውን ኃይል በመጠቀም እየታገሉ መሆናቸውን አስታውሰው " በኃይል አለመመጣጠን ምክንያት ጊዜያዊ ወታደራዊ ብልጫ ስላገኙ ይህንን ሚዛን ለመለወጥ የመመከት ትግላችንን አጠናክረን እያስቀጠልን እንገኛለን።" ብለዋል።

ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በጠቀሱት ትግል "ከፍተኛ ዋጋ ጠይቋል" ያሉ ሲሆን። "የህወሃት መስራች አባላት ከሚባሉት ላለፉት 45 ዓመታት ከያዙት ህዝባዊ መስመር ፈቀቅ ሳይሉ የታገሉና የመሩ፣ ያታገሉና ብዙ ድል ያስመዘገቡ አዛውንት ነባር ታጋዮች በዚህ የወረራ ጦርነት፣ በጠላት እጅ ተጎድተውብናል። ከባድ መስዋዕትነት ከፍለዋል። አሁንም እየከፈሉ ይገኛሉ። የነዚህ ጀግኖቻችን መስዋዕትነት የበለጠ ቁጭትና እልህ ያስንቀናል እንጂ ፈፅሞ ከትግላችን የሚያቆመን አይሆንም።" ብለዋል።

"እኛ ከመሬታችን እና ከቀያችን ለቀን የምንሄድበት ሌላ ቦታ የለንምና የተሟላ ድል እስክንቀዳጅ ህዝባዊ ጦርነት ከማፋፋም ወደ ኋላ እንደማንል ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል።" በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል።

የደብረ ፅዮንን ንግግር በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

(Via BBC Amharic)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news