Get Mystery Box with random crypto!

ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የገቢዎች ሚኒስቴር ፤ ከጥር 14 እስከ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 64,025,470.75 ብር ግምተዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ወደ ሀገር ለማስገባት እና ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የገለጸው፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋ 48,382,510.75 ብር ሲሆን 17,642,960 ብር የሚገመት የወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ ኬላዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል መድኃኒት፣ የምግብ
ምርቶች ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የትምባሆ ውጤቶች ፣ አደንዛዥ ዕፆች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡

ዕቃዎቹን በጉምሩክ ሰራተኞች ፣ በፀጥታ አካላት እንዲሁም በህብረተሰቡ ርብርብ መያዝ መቻሉን ብስራት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባገኘነው መረጃ ተመላክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news