Get Mystery Box with random crypto!

የህዳሴው ግድብ ያለበት ሁኔታ ተገመገመ። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እና በሚፈለ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የህዳሴው ግድብ ያለበት ሁኔታ ተገመገመ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ቦርድ አባላት በስፍራው በመገኘት መገምገማቸውን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።

በግምገማው መሰረትም የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ እንደሆነና የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ሚንስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑ ኮንትራተሮች፣ ከባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ለግድቡ መጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውስጥ እና ውጪ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከምን ግዜው በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news