Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስናት ፈጋግ ድንበር ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ ሥራ ጀመረ! የኢ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስናት ፈጋግ ድንበር ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ ሥራ ጀመረ!

የኢሚግሬሽን ፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስናት የጋምቤላ ክልል ፈጋግ ድንበር የመጀመሪያው ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ ትናንት በማስመረቅ ሥራ ጀመረ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክታር አቶ ሙጂብ ጀማል በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ወቅት እንዳሉት የመቆጣጠሪያ ኬላው የሁለቱ ሀገራትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል።

በተለይም በአካባቢው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና አሁን ላይ የሀገራት ስጋት የሆነውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ጭምር ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ እያስከተለ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ኤጀንሲው ከ2012ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ ጠረፋማ አካባቢዎች ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላዎችን በማቋቋም ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና ፍልሰትን ለመቆጣጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news