Get Mystery Box with random crypto!

በትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ። በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን 'ሰዴ ሙጃ ወረዳ' | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን "ሰዴ ሙጃ ወረዳ" በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍል ገለፀ።

መነሻውን ከባሕር ዳር ያደረገው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሰዴ ሙጃ ወረዳ ሲደርስ 200 ሜትር ከሚረዝም ገደል በመግባቱ ነው የ24 ሰዎች ህይወት ያለፈው።

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በደብረ ታቦር እና በፈለገሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ አብመድ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news