Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ አዲስ ማለዳ ከምክር ቤቱ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 29/2015 ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ያጸድቃል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news