Get Mystery Box with random crypto!

ትግራይ በትግራይ ክልል ረሃብ 'በከፍተኛ መጠን' መጨመሩን ተመድ አስታወቀ!! በጦርነት በተጎዳ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ትግራይ

በትግራይ ክልል ረሃብ 'በከፍተኛ መጠን' መጨመሩን ተመድ አስታወቀ!!

በጦርነት በተጎዳው የትግራይ ክልል ለከፋ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እና፣ በቅርቡ የምግብ ርዳታ መቆሙን ተከትሎ፣ ሁኔታዎች እየተባባሱ ሊሄዱ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ፤ሰኞ ዕለት ይፋ ባደረገው ወቅታዊ ሪፖርት፣ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨማሪ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚኖሩ 8.8 ሚሊየን ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news