Get Mystery Box with random crypto!

#አጭር_ልብወለድ #'እሽሩሩ_መዉደድ---_እሽሩሩ ፍቅር' #ክፍል.....2 ማሕሌት እና ባልኮ | ልብወለድ Ethio_Fiction

#አጭር_ልብወለድ

#"እሽሩሩ_መዉደድ---_እሽሩሩ ፍቅር"

#ክፍል.....2

ማሕሌት እና ባልኮኒዉ ጋ ተቀምጦ ቢራ ሲጠጣ የነበረዉ ቋሚ ደንበኛዋ አበራ ዳንስ ወለሉ ላይ ወጥተዉ በባህር ማዶ ዘፈን ተቃቅፈዉ መደነስ  ጀምረዋል፡፡ ማሕሌት ያን ታላቅ ዳሌዋን እያዉረገረገች፡፡ የሁሉም ሰዉ ዐይን እነሱ ላይ ነዉ፡፡
    
ከዉጪ ሪዛሙ ሸበላ ገብቶ ፊት ለፊቴ ከሚገኘዉ ቦታ ላይ ተቀመጠ፡፡ ረጅም ነዉ፣ መልከ መልካም፡፡ የቀይ ፊቱን ሰፊ ወሰን የሸፈነዉ ሪዙ መጀመሪያ ቀን መጥቶ ካየሁት ጥቂት በመጎፈሩ ሳይሆን አይቀርም ግርማዉን አግንኖታል፡፡ የተቀመጠዉ ከባልኮኒዉ ጥቂት ራቅ ብሎ ካለዉ ቦታ ነዉ፡፡ የሆነ ገፅታዉ ከቀድሞ ፍቅረኛዬ ጋር ይመሳሰላል፣ አፍንጫዉ፣ የትከሻዉ ስፋት፣ የከናፍሩ ስስነት ምናምን፡፡