Get Mystery Box with random crypto!

#የቀጠለ በዐይን ቋንቋ ተነጋግሮ ትኩረት ለመሳብ የሸበላዉ ዐይኖች ወደ እኔ የሚወረወሩበትን አጋጣ | ልብወለድ Ethio_Fiction

#የቀጠለ
በዐይን ቋንቋ ተነጋግሮ ትኩረት ለመሳብ የሸበላዉ ዐይኖች ወደ እኔ የሚወረወሩበትን አጋጣሚ በቋፍ እየጠበቅሁ ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ፣ ሸበላዉ ዐይኑን ሄለን ላይ ተክሏል፡፡ ቀልቡ ሳይወዳት አልቀረም፡፡ እዚህ ቡና ቤት ከምንሠራዉ ጋለሞቶች ብዙ ደንበኛ ያላት ሄለን ናት፡፡ ሄለን ከእኔ የባሰች ጋግርታም ብትሆንም በሰዉ የመወደድ ፀጋን የታደለች የጠይም ቆንጆ ናት፡፡ ቀዝቃዛነቷ ስትፈጠር ጀምሮ የተጣባት ይሁን ዘግይቶ የተከሰተ በዉል አይታወቅም፡፡ ዉበቷ ነዉ ድብርቷን ሸፍኖ ዓለም መኖሯን እንዳይዘነጋ የረዳት፡፡ ብዙ ጊዜ እኛ ሥራ አጥተን ጦማችንን ስናድር እሷ ወንድ አማርጣ ትወጣለች፡፡ ሄለን ሐሜት ልብሷ ነዉ፤ ቡና ቤቱ ዉስጥ የእሷ ስም ሳይብጠለጠል ቀርቶ አያዉቅም፡፡
ሸበላዉ ዐይኖቹን ከሄለን ላይ ነቅሎ ወደ እኔ ሲወረዉር ዐይን ለዐይን ተጋጨን፣ ተሽኮርምሜ ዐይኖቼን ሰበርኩ፡፡ እንደገና ባልኮኒዉ ዙሪያ የጦፈዉን ሁካታ የምከታተል መስዬ በስላቺ ስሰልለዉ አሁንም ዐይኖቹን እኔ ላይ እንደሰፋ ነዉ፡፡ ሸበላዉ ሴት አዉል ይመስላል፡፡

የባልኮኒዉን ትዕይንት መታዘብ ትቼ ወደ ሸበላዉ ሳማትር አዜብ ፊቱ ተገትራለች፣ እነዛን አንደ ኮርማ በሬ ቀንድ ከርቀት የሚታዩትን ጡቶቿን ወድራ፡፡ ያለ ወትሮዋ ደርሳ አስተናጋጅ መሆኗ ደንቆኛል፡፡          ጎኔ ካለዉ ጠረጴዛ (በግራዬ በኩል) ጥንዶች ተቀምጠዋል፡፡ ወንድየዉ ፀጉሩን ድሬድ ሎክ ተሠርቷል፡፡ ሙሉ ቀልቡን አብራዉ ካለችዉ ሴት ጋር ያደረገ ቢመስልም በአይኑ ቂጥ እኔን ሰርቆ ማየቱን አላቆመም፡፡                        
ሸበላዉን እየሰረቅሁ መመልከቴን ቀጥያለሁ፡፡ ቢራ የተሞላ ብርጭቆዉን አንስቶ ወገቡ ድረስ ተጎነጨና ሲጋራዉን ምጎ ጭሱን አየር ላይ ተፍቶ ቡሹን ሲጋራ መተርኮሻዉ ላይ ደፈጠጠ፡፡ አዜብ ቢራ ካቀረበችለት በኋላ እንኳ ከሦስቴ በላይ ወደ እሱ ተመላለሰች፡፡ ቀልቡ ሳይጠላት አልቀረም፤ እንጂማ ወንበር እንድትጋራዉ ጠይቆ ቢራ ይጋብዛት ነበር፡፡ ከስፒከሩ የፍራንክ ሴናትራ መረዋ ድምፅ መንቆርቆሩን ቀጥሏል፡፡
ሸበላዉ ዐይኖቹን ዳንስ ወለሉ ላይ ተክሏል፡፡ የእነ ማሕሌት ዳንስ የመሰጠዉ ይመስላል፡፡ ዐይኖቹን ከዳንስ ወለሉ ላይ ትዕይንት ላይ ሳይነቅል ሁለተኛ ሲጋራዉን አቀጣጠለ፡፡ ጎኔ የተቀመጡት ጥንዶች የጦፈ ወግ አለሁበት ድረስ ጎልቶ ይሰማል፣ ጆሮዬን ጥዬ የሚሰልቁትን ወግ ማዳመጥ ጀመርኩ፡  

“ኧረ እባክህ! በጣም ይገርማል! ምን አፋታቸዉ?” ሴቷ፡፡
“ምን እባክሽ፣ እሱ መች ይረባል፡፡ ያቺን የመሰለች ልጅ …” ወንዱ፡፡ ከፊል የፊቱ ገፅ ብቻ ነዉ የሚታየኝ፡፡ ትከሻ ሰፊ ነዉ፡፡ 
 “እንዴት አወቅክ አንተ?”  
 “የድሮ ወዳጄ አልነበር እንዴ?”
“ዉሻ ነዉ ለካ አንተ?”
“እየነገርኩሽ! እሱ አመሉ ነዉ፣ በአንድ አይረጋም፡፡ ዛሬ ከአንዷ ጋር አይተሽዉ ከሆነ ነገ ከሌላዋ ጋር ታገኝዋለሽ፡፡ እሚገርምሽ እኮ ከበፊቷ አንድ ወልዷል፡፡”
“ይገርማል! ግን እኮ አንደዛ አይነት ሰዉ አይመስልም፡፡”  
“ቢራ ይጨመራ? ጠጪ እንጂ!” አጨብጭቦ አስተናጋጇን ጠራ፡፡
“እንዴ ይብቃን! ልታሰክረኝ ነዉ እንዴ አላማህ? በዚያ ላይ መሽቷል፡፡”
“እንጫወት እንጂ፣ ገና እኮ ነዉ?”
“ምን ማለትህ ነዉ? ባለትዳር መሆኔን ረሳኸዉ? አንተን ብዬ እንጂ …?”
“ተይ እንዲህ አትበይ፡፡ ምንም ቢሆን የመጀመሪያሽ እኮ እኔ ነኝ፡፡”
“እኔስ አንተን ብዬ መስሎኝ ኃጢያት ዉስጥ የገባሁት፡፡ ተረዳኝ እንጂ!”      
ፊት ለፊቴ የተቀመጠዉ ሪዛም ሸበላ ዐይኖቹን ከነ ማሕሌት ላይ አሽሽቶ ወደ እኔ ሲዞር ለሁለተኛ ጊዜ ዐይን ለዐይን ተጋጨን፣ ቀድሜ ዐይኖቼን ሰበርኩ፡፡ ከጎኔ ያሉት ጥንዶች የሚቀዱት ተባራሪ ወሬ አሁንም በጆሮዬ መስረጉን ቀጥሏል፡፡
“ማመን ይከብዳል! እዉነትህን ነዉ? እሷስ እንዴት እሽ አለች?” ሴቷ፡፡
“አንቺ ደግሞ፣ ሰዉየዉ እኮ ዮናስ ነዉ፡፡ ምን ነካሽ?” ወንዱ፡፡
“ኧረ እባክህ? አሳምኗት ነዉ አየህ?”
“ምላሱ ጤፍ ይቆላል ስልሽ!”

ማሕሌት እና አበራ አዲስ የተከፈተዉን ዘፈን ምት ተከትለዉ ተቃቅፈዉ መደነሱን ቀጥለዋል፡፡ የማሕሌት ቁመት ከአበራ ስላጠረ ጎበጥ ብሎ ሊያቅፋት ተገዷል፡፡

#Inbox @Faraw_sam

#share @ethio_fiction