Get Mystery Box with random crypto!

#አጭር ልብወለድ 'እሽሩሩ መዉደድ--- እሽሩሩ ፍቅር' ክፍል.....1 ሳባ እባላለሁ፡፡ ቅፅል | ልብወለድ Ethio_Fiction

#አጭር ልብወለድ

"እሽሩሩ መዉደድ--- እሽሩሩ ፍቅር"

ክፍል.....1

ሳባ እባላለሁ፡፡ ቅፅል ስሜ ጁሊ፡፡ እነሆ ዕጣ ፈንታ ካዛንቺስ የተባለ ሲኦል መንደር ወርዉሮኝ አበሳ የበዛበት የቡና ቤት ኑሮን መግፋት ከጀመርኩ ዓመታት አለፉ፡፡ የመከኑ ግን ታሪኬ ሲተረተር አብረዉ የሚወሱ (እኔ ለሌሎች ስተርክ ሳንሱር አድርጌ የምዘላቸዉ) ድፍን ሦስት ዓመታት፡፡ እዚህ ሮማን ቡና ቤት አብረዉኝ ከሚሠሩት ሴቶች ተገንጥዬ ጥጌን ይዤ ቢራ እየጨለጥኩ ተጎልቻለሁ፣ ግንባሬ ጎትቶ የሚያመጣልኝን ወንድ በቋፍ እየጠበቅኩ፡፡ እንደ ሁልጊዜዉ ጥቁር አጭር ቀሚስ ነዉ የለበስኩት፡፡ አብዛኛዉ ልብሴ ጥቁር ነዉ፡፡ ጥቁር ጨርቅ የጠይም ገላዬን ዉበት እንደሚያጎላዉ አዉቃለሁ፡፡ ከሁለት ቀን በፊት ብቅ ብሎ የነበረዉ ረጅም ሪዛም ሸበላ (ቀልቤን ሰርቆ የሄደዉ ሸበላ) ዐይኑን እንዲሁ ገላዬ ላይ ሲያንከራት አመሸ፣ ቤቱን ያ ሁሉ ቆንጆ ሴት ሞልቶት ሳለ፡፡