ለ60 አመታት እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም የሚሉት የ80 አመት አዛውንት ቬትናማዊው ታይ ንጎክ በ20 አመታቸው ከገጠማቸው ከባድ ህመም በኋላ ከእንቅልፍ ጋር መለያየታቸውን ይናገራሉ።
የህክምና ባለሙያዎች ግን አዛውንቱ ምናልባት ስለማይሰማቸው እንጂ በቀን ውስጥ የተወሰኑ ስአታት መተኛታቸው አይቀርም ባይ ናቸው።
የሰው ልጅ አይደለም ለአመታት ለጥቂት ቀናት የእንቅልፍ መዛባት ከገጠመው በጤናው ላይ ምን ይዞ እንደሚመጣ መገመት አይከብድም።
ከወደ ቬትናም የተሰማው ዜና ግን ለአመታት መነጋገሪያ ሆኖ ዘልቋል።
በዚህ አመት 80ኛ አመታቸውን የያዙት ታይ ንጎክ፥ ላለፉት ስድስት አስርት አመታት እንቅልፍ ይዞኝ አያውቅም ይላሉ።
ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና ጎረቤቶቻቸውም ጭምር ንጎክ ተኝተው አይተዋቸው እንደማያውቁ ነው የሚገልጹት።
አዛውንቱ በፈረንጆቹ 1962 (የ20 አመት ወጣት እያሉ) ከገጠማቸው ህመም ወዲህ ከእንቅልፍ ጋር ተሰነባብተዋል።
#ዘገባው - የአል-ዐይን ነው
#Inbox - @Faraw_sam
#share - @ethio_fiction