Get Mystery Box with random crypto!

በሕንድ ሚስቱ የማገጠችበት ባል የፈጸመው ድርጊት አነጋገረ በሩቅ ምስራቋ ሕንድ አስገራሚ የትዳር | ልብወለድ Ethio_Fiction

በሕንድ ሚስቱ የማገጠችበት ባል የፈጸመው ድርጊት አነጋገረ

በሩቅ ምስራቋ ሕንድ አስገራሚ የትዳር ገጠመኝ የተከሰተ ሲሆን ዜናው ከሕንድ አልፎ መላው ዓለምን አዳርሷል፡፡
ፈጠራ እንጂ በእውኑ ዓለም ሊያጋጥም አይችልም የተባለው ይህ የሕንድ ባልና ሚስቶች ታሪክ እንዲህ ይጀምራል።

ኒራጅ እና ሩቢ የተሰኙ ህንዳዊያን በፈረንጆቹ 2009 ላይ ነበር ጋብቻቸውን የመሰረቱት፡፡ እነዚህ ባልና ሚስቶች በአብሮነት ቆይታቸው አራት ልጆችንም ወልደዋል ተብሏል፡፡

ኒራጅ ባለቤቱ ሩቢ ሙከሽ ከተሰኝ ሌላ ህንዳዊ ወንድ ጋር የድብቅ ፍቅር መጀመሯን ይደርስበታል፡፡ ይህች የልጆቹ እናትም የጀመረችውን የድብቅ ፍቅር እንደደረሰበት እና እንድታቋርጥ ይጥራል፡፡ ይሁንና የኒራጅ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቶ ከሙከሽ ጋር ለመጠቃለል መብቃቷን ይረዳል፡፡

ሚስቱን ያጣው ኒራጅም ወደ አካባቢው ተመልሶ ሽማግሌዎች መላ እንዲፈልጉለት ይማጸናል፡፡ የሀገሬው ሽማግሌዎችም ሩቢ ወደ ቀድሞ ባሏ እንድትመለስ ውሰኔ ቢያስተላልፉም ኒራጅ ግን ሚስቱን መልሶ ማግኘት እንዳልቻለ ተገልጿል፡፡

ሚስቱን ያጣው ኒራጅም ሶስተኛ አማራጭ ለመፈለግ መገደዱ የተገለጸ ሲሆን ሚስቱን የቀማው ሰው ሚስት ጋር መቀራረብን እንደ አማራጭ ለመውሰድ መገደዱን ኢንዲያ ቱዴይ ዘግቧል፡፡
ሩቢ የሚል ተመሳሳይ ስም እንዳላት የተገለጸችው ይህች ሴትም እንደ ኒራጅ በባለቤቷ ማታለል ተፈጽሞባታል፡፡
በመጨረሻም እነዚህ በፍቅር የተገፉ ወንድ እና ሴትም ለመጋባት መብቃታቸው የተገለጸ ሲሆንከዚህ በፊት የተወለዱ ልጆቻቸውንም ለመቀበል ወስነዋል ተብሏል፡፡፡

ይሁንና በትዳራቸው ላይ የማገጡት ሙከሽ እና ሩቢ ግን በቀረበባቸው ወንጀል ምክንያት በፖሊስ በመፈለግ ላይ እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

#አጃኢብ_ነው

#Share - @ethio_fiction