Get Mystery Box with random crypto!

#የቻይና ሳይንቲስቶች የተራራቁ ፍቅረኛሞች መሳሳም የሚያስችል ማሽን መስራታቸውን ገለጹ:: የተራራ | ልብወለድ Ethio_Fiction

#የቻይና ሳይንቲስቶች የተራራቁ ፍቅረኛሞች መሳሳም የሚያስችል ማሽን መስራታቸውን ገለጹ::

የተራራቁ ፍቅረኛሞችን ለማቀራረብ ይውላል የተባለው ይህ ማሽን በቻንግዙ የቴክኒክ ሙያ መምህራት እንደተሰራ ተገልጿል።
ቻይናዊያን ግን በአዲሱ ፈጠራ ዙሪያ አድናቆትን እና ትችቶችን በመሰንዘር ላይ ናቸው
የቻይና ሳይንቲስቶች ተራራቀው የሚኖሩ ፍቅረኛሞች መሳሳም የሚያስችል ማሽን መስራታቸውን ገለጹ።

በሀገረ ቻይና ያሉ የቴክኒክ እና ሙያ መምህራን ተራርቀው ለሚኖሩ ፍቅረኛሞች መፍትሔ አለን ብለዋል።
መምህራኑ የሰሩት ማሽን የአንድን ሰው የከንፈር ትክክለኛ ጣዕም ለሌላኛ ሰው ማስተላለፍ የሚያስችል እንደሆነ ሲኤንኤን የቻይናውን ግሎባል ታይምስ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አገልግሎቱ አንድ ሰው ይህን ማሽን ወደ አፉ አስጠግቶ በመሳም ከዚያም ወደ ሚፈልገው ወይም ወደ ምትፈልገው ሰው የራሱን መሳም ወደ ማሽኑ በመጫን መላክ ያስችላል ተብሏል።
ይህ ማሽን አሁን ላይ በመላው ቻይና ባሉ የገበያ ቦታዎች በ37 ዶላር በመሸጥ ላይ ነው የተባለ ሲሆን ማሽኑ አድናቆትንም ትችቶችንም በማስተናገድ ላይ ነው።

አንዳንዶች ማሽኑን በሰሩት የቻንግዙ ሜካትሮኒክ ቴክኖሎጂ መምህራን አድናቆታቸውን ሲገልጹ ሌሎቹ ደግሞ ማሽኑ ምንም ጥቅም እና ስሜት የማይሰጥ ፈጠራ እንደሆነ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየጻፉበት ነው ተብሏል።
መምህራኑ ማሽኑን ከአራት አመት በፊት እንደሰሩት ገልጸው በፈረንጆቹ 2019 ላይ ደግሞ የፈጠራ ባለቤትነት መብት ማግኘታቸው ተገልጿል።

#ምንጭ:- አል-ዐይን News

#መልካም_ምሽት

#share : @ethio_fiction