Get Mystery Box with random crypto!

'ደካማ ነው፣ ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ አድርሰነዋል' የተባለው ኦነግ ሸኔና. እንቅስቃሴው፤ የተ | ልብወለድ Ethio_Fiction

"ደካማ ነው፣ ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ አድርሰነዋል" የተባለው ኦነግ ሸኔና. እንቅስቃሴው፤ የተጣጣመ አይደለም።
“ደካማ አይደለሁም” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የፈለገ በሚመስል መልኩ ነው አረመኔያዊ ተግባሩን እየፈጸመ የሚገኘው፡፡  

ከአራት ቀን በኋላ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በምዕራብ ወለጋ ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የፈፀመው አሰቃቂ ግድያ፣ በእልህና በበቀል ስሜት የተሞላ ይመስላል፡፡ ንጹሃንን ከህጻን እስከ አዋቂ በጅምላ ነው የጨፈጨፈው፡፡
ቶሌ ቀበሌ በስሩ ጉቱ፣ ጨቆርስ፣ ሳልሳው እና በገኔ የሚባሉ መንደሮች አሉ። ነዋሪዎቹ የደርግ መንግስት በወቅቱ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች አምጥቶ ያሰፈራቸው ናቸው፡፡ ያለፉትን ስልሳ ዓመታት ያሳለፉት በማረስና ለክልሉ መንግስት በመገበር ነው፡፡ በአጭር አገላለፅ ንፁህ ሲቪል ሰዎች ናቸው ማለት ነው፡፡ እነዚህ ከአፈር ጋር ታግለው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ የተጨፈጨፉት፡፡

ሰባት ሰዓት በወሰደ ጥቃት ከ500 የማያንሱ ሰላማዊ ዜጎች (ህጻናት፣ ሴቶችና በእድሜ የገፉ አዛውንቶችን ጨምሮ) መገደላቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ለቶሌ ሟቾች የህሊና ፀሎት እንዲደረግ፣ በጉዳዩ ላይም ም/ቤቱ እንዲወያይበት በማለት በአብን አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፤ “ቀድሞ ባልተያዘ አጀንዳ አንነጋገርም” በማለታቸው ምክር ቤቱ በችግሩ ላይ ሳይነጋገር፣ የህሊና ፀሎትም ሳያደርግ ቀርቷል፡፡ አንድም የምክር ቤት አባል ቢያንስ ቢያንስ የህሊና ጸሎቱን ደግፎ ሲናገርም ማየት አልተቻለም፡፡ ከሰብአዊነት ይልቅ የፖለቲካ ሰውነታቸው የጠናባቸው የምክር ቤቱ አባላት፤ እንዴት የዜጎች ሞት አላስጨነቃቸውም? ይህም ጥያቄ ነው፡፡

Share ---->
@ethio_fiction

#መልካም_ቀን