Get Mystery Box with random crypto!

' ...ታላላቅ ኃይላት ጸጥ ያሉ ናቸው :: የመሬት ስበት ጮኾ ያውቃል !? ፀሐይ አጓርታ ታውቃ | ልብወለድ Ethio_Fiction

" ...ታላላቅ ኃይላት ጸጥ ያሉ ናቸው ::

የመሬት ስበት ጮኾ ያውቃል !? ፀሐይ አጓርታ ታውቃለች !? ዛፍ በቁመት ሲያድግ ድምጽ አለው !? ኤሌትሪክ በኮረንቲ ውስጥ ሲያልፍ ይሰማል !? የቢሊዮኖች የሳምባ ትራፊ ካርበን ዳይኦክሳይድ ወደ እስትንፋስ ግብአታችን ሲቀየር የማሽኖች ኳኳታ ያሰማል !?

ዝምታ ግዝፈቱ አይታወቅም ። ዝምታ ትንሽ አይደለም :: ቀና ብሎ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ የተዘረጋውን ጠፈር ላስተዋለ ሰው ዐይኑ የተመለከተውን ጠለል ጆሮው ግን አይሰማውም ዝምታ ትልቅ ብቻ አይደለም በጥቃቅን ረቂቅ መስተጋብሮችም ውስጥ የዝምታ ሚስጥር ተቀብሯል ።

ሚሊዮን እና ሚሊየኖች የሰውነታችን ህዋሳት እልፍ ቦታ ይካፈላሉ ይራባሉ ይላላካሉ ይዋጋሉ ይገድላሉ ይሞቱማል ። አያማርሩም አያቃስቱም አይነጫነጬም በዝምታ ይመላለሳሉ ::

በዝምታ ማስተንተን የህይወትን ጣፋጭ መቅኔ እንደመምጠጥ ነው :: "

" አርምሞ "
በዶክተር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ
አስራ አምስተኛ ዕትም
/ ጋብሬላ


Share ---> @ethio_fiction