Get Mystery Box with random crypto!

አገሬ ያንቺ ቅኔ፤ አይፈቱት ደረሰ ችግኝ  ይተከላል፤ ሰው እየፈረሰ “ይባስ አታምጣ”፤ ብዙ ክፉ ነ | ልብወለድ Ethio_Fiction

አገሬ ያንቺ ቅኔ፤ አይፈቱት ደረሰ
ችግኝ  ይተከላል፤ ሰው እየፈረሰ
“ይባስ አታምጣ”፤ ብዙ ክፉ ነገር የገጠማቸው ሰዎች የሚያደርሱት ፀሎት ነው፡፡

#ትውስታ
ሻሸመኔ ከተማ ላይ ሰው ተዘቅዝቆ ሲሰቀል የከተማው ነዋሪዎች ይባሰ አታምጣ ብለው ፀልየው ሊሆን ይችላል፡፡

ለፖለቲካ አላማና ግብ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተገደለ ጊዜ፣ ሻሸመኔ በአጥፊዎች ከመወረር አልዳነችም፡፡ ነዋሪዎቿ ቀደም ብሎ በተዘጋጀ ዝርዝር ስማቸው እየተጠራ፣ እምነታቸው እየታየ ከመገደል አልተረፉም፡፡

ዝዋይ፣ አጋርፋ፣ አሩሲ ነገሌ እና ሌሎችም ከተሞች እንዳልነበሩ የሆኑት፣ በህይወት የተረፉትም በአንድ ቀን ወደ ፍጹም ድህነት የተለወጡት "ክፉ አታሳየን" ብሎ የሚፀልይ ጠፍቶ ሳይሆን፤ ክፉን የሚያጠፋ መንግስት ጠፍቶ ነው፡፡ ከክፉዎቹ አንዱ ደግሞ በማይታይና በማይገለጥ ተንከባካቢ ኃይል እየተጠበቀና እየታገዘ ያለው፣ የተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ብሎ የፈረጀው "ኦነግ ሸኔ" ነው፡፡