Get Mystery Box with random crypto!

“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ 'ተቋም' እንደሌለ የትምህርትና | ሰበር !!



“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ 'ተቋም' እንደሌለ የትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን አሳውቋል።

የትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መቋቋም የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 እንዲሁም በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 መሰረት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል መጠሪያ ግንቦት 29/2014 ዓ.ም እንደተቋቋመ በመግልጽ በማህበራዊ ድረ-ገጽ እየተዋወቀ የሚገኝው "ተቋም" እውቅና የሌለው መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በማለት ራሱን እያስተዋወቀ የሚገኘው "ተቋም"፤ ከባለሥልጣኑ ምንም አይነት ፈቃድ ያልተሰጠው እንደሆነ ተመላክቷል።

በቀጣይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ ባለስልጣኑ አሳውቋል።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝