Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር !!

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiio_students — ሰበር !!
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiio_students — ሰበር !!
የሰርጥ አድራሻ: @ethiio_students
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 613
የሰርጥ መግለጫ

ℹ ይህ ትክክለኛና ወቅታዊ የትምህርት ዜናዎች በየጊዜው የሚቀርብበት ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ ነው
🔸መረጃ እና መልዕክት ለመላክ 📧 @Ethiiostudents_bot
🔸ሼር ማድረጊያ ሊንክ 🔗 @ethiio_students
ኢትዮ students ✔️

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 13:58:26
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ታብሌቶች ካልደረሱ ሌሎች አማራጮች እንደሚጠቀም መንግስት አስታወቀ!!

በሚቀጥለዉ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች በወቅቱ ካልደረሱ ሌሎች ምርጫዎችን መንግስት ይከተላል-ጠ/ሚ አብይ

በ2015 ዓ.ም የሚሰጠዉ ሀገር አቀፍ ፈተናን ዲጂታል በሆነ መንገድ በኦንላይን ምዘናዉን ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል። ለዚህም 1ሚሊዮን የሚሆኑ ታብሌት ኮምፒውተሮች ወደ ሀገር ይገባሉ ተብሎም ነበር።

ጠ/ሚ አብይ ይህን በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ ያለዉን ስርቆት ለማስቀረት ሲባል ፈተናዉን ዲጂታላያዝ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም 1ሚሊዮን ታብሌት ኮምፕዩተሮቹን ከቻይና መንግስት ጋር በመሆን ለማስገባት እየተሰራ እንደነበር አስታዉሰዋል። ሆኖም በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያትም አምራች ድርጅቱ ስራዉን በተያዘለት ግዜ ማጠናቀቅ አለመቻሉን አስታዉቀዋል።

በ2015 ለመስጠት የታቀደዉ ፈተናዉ ፤ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ ታብሌት ኮምፒውተሮቹ በተያዘላቸዉ ግዜ ከደረሱ ፈተናዉ ይሰጣል ብለዋል። ሆኖም ታብሌቶቹ በግዜዉ ካልደረሱ መንግሰት ሌሎች ምርጫዎችን እንደሚጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
1.8K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:04:43
በአማራ ክልል የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ለሦሥት ቀናት ይሰጣል ተብሏል።

በክልሉ ከ359 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ፈተናው በክልሉ በሚገኙ 5 ሺህ 395 ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ መምህራን ፈተናውን በመስጠት ይሳተፋሉ።

የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር እና በሐረሪ ክልሎች ትላንት መሰጠት ጀምሯል።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
3.7K views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 13:19:31
G_12

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል ?

የትምህርት ሚኒስቴር የብሄራዊ ፈተና መሰረቅንና ኩረጃን ለመከላከል ፈተናው በኦንላንይ መስጠት እስኪጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

የፈተናውን አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም የ2014 ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20 / 2015 ዓ/ም በኃላ እንደሚሰጥ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም ፤ እስካሁን ድረስ የተቀየረም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለፀ አዲስ ነገር የለም።

ከትላንት ጀምሮ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተናው ሃምሌ እና ነሃሴ ላይ ነው የሚሰጠው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ ያልታወቀና ሀሰተኛ በመሆኑ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በጥናታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ወላጆችም ልጆቻችሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እገዛችሁን እንድታጠናክሩ ይሁን።

እጅግ በርካታ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች የሚከታተሉት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ የሚወጡ መረጃዎችን አምናችሁ አትቀበሉ። አንድን መረጃ ስትሰሙ ከትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን አረጋግጡ።

#share
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students
6.7K viewsedited  10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 11:50:46
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ብሄራዊ ፈተና ምዝገባ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2014 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል ብሄራዊ ፈተናውን የምትፈተኑ ተማሪዎች እስከ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን እስካሁን ሳትመዘገቡ ለቀራችሁ ተፈታኝ ተማሪዎች በቀረው ጊዜ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡ በየደረጃው የምትገኙ የትምህርት አመራሮች በተለይም የት/ቤት ር/መምህራን ተፈታኝ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን ጥረት እንድታደርጉ እየጠየቅን፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ችግር አገልግሎቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ይገልጻል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
8.6K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 14:40:28 #NEAEA

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ብሄራዊ ፈተና ምዝገባ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2014 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል ብሄራዊ ፈተናውን የምትፈተኑ ተማሪዎች እስከ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን እስካሁን ሳትመዘገቡ ለቀራችሁ ተፈታኝ ተማሪዎች በቀረው ጊዜ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡

በየደረጃው የምትገኙ የትምህርት አመራሮች በተለይም የት/ቤት ር/መምህራን ተፈታኝ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን ጥረት እንድታደርጉ እየጠየቅን፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ችግር አገልግሎቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
7.0K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 10:44:50 Do you enjoy reading this channel?

Perhaps you have thought about placing ads on it?

To do this, follow three simple steps:

1) Sign up: https://telega.io/c/ethiio_students
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
7.8K viewsedited  07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 14:27:17 በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የስራ ኃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ 49 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ ባልተገባቸው የእድገት ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ተብለው ከተጠረጠሩት ሰባ የመንግስት ሰራተኞች መካከል አርባ ዘጠኙ ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

በመምሪያው የጸረሙስና እና ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዋና ሳጅን ደርባባ ቶሎሳ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በተለያዩ የወረዳ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በሃላፊነት ቦታ ላይ ከሚገኙት ውስጥ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም ተገልጿል፡፡

በዞኑ እየተደረገ ባለው ማጣራት እሳከሁን የጤና ፣የትምህርት፣ የመሬት ፣የመንጃ ፍቃድ እንዲሁም ሌሎች ሀሰተኛ ሰነዶች በተመሳሳይ መሰራታቸው በፍትህ አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑም ተነግሯል ፡፡

በመሆኑም የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስካሁን በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ በተደረገው ምርመራ ከተጠረጠሩት ሰባ ሰራተኞች መካከል አርባ ዘጠኙ ላይ ከሁለት አመት እስከ አራት ዓመት እስራት እንዲሁም ከአስር ሺህ ብር እስከ ሃምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መወሰኑን ዋና ሳጅን ደርባባ ቶሎሳ ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
7.7K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 10:40:38
እውቁ ካናዳዊ አቀንቃኝ ግማሽ ፊቱ ፖራላይዝ አንደሆነ ተናገረ

እውቁ የዘፈን ደራሲና አቀንቃኝ ጀስቲን ቢበር ከፊል ፊቱ ፓራላይዝድ እንደሆነ ተናግሯል።

ጀስቲን 240 ሚሊዮን ተከታዮች ባሉት ኢንስታግራሙ ላይ በለቀቀው ቪድዮ “እንደምታዩት ይህኛው ዓይኔ አልገለጥ ብሏል፤ በዚህኛው የፊቴ ክፍል ፈገግ ማለት አልችልም፤ ያኛው የፊቴ ክፍል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ፓራላይዝድ ሆኗል” ሲል ተደምጧል።
በዚህም ‘ጀስቲስ ወርልድ ቱር’ በሚል በተለያዩ ሀገራት ኮንሰርት ሲያርባቸው ከነበሩ ኮንሰርቶች ስስቱን ሰርዞ ለሌላ ጊዜ ማሸጋገሩን ዘ-ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለማገገም የተቻለውን የአካል እንቅስቃሴ እንደረገ መሆኑ ጀስቲን ቢበር ለአድናቂዎቹ ጸሉይልኝ በማለት መልእክት አስተላልፏል፡፡

ከጀስቲን ቢበር ነገሮች ድንቅ እሚለኝ ነገር ከኮንሰርቶቹ በፊትና በኃላ ቲሙን ሰብስቦ ለፈጣሪው ምስጋና ሲያቀርብ ብዙ ግዜ ተመልክቸዋለሁ በሌሎች አርቲስቶች በተለይ በምዕራብያኑ አርቲስቶች ይህ ነገር እንብዛም አልተለመደምና ጀስቲን ቢበር ፈጣሪውን የማመስገን ድርጊቶቹ ድንቅ ነው ዛሬም በኢንስታግራሙ ባስተላለፈው መልክት ደጋግሞ ከበሽታው እንዲፈወስ አድናቂዎቹን ጸልዩልኝ ሲል ይሰማ ነበር
Via natnael_mekonen

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
7.3K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:23:28
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና የሰጠው ት/ቤት !

በሀገር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና መስጠቱን የአረካ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታዉቋል።

ይህም ሀገራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ የቴክኖሎጂ ችግር እንዳይገጥማቸው ያግዛል ነው የተባለው።

ፈተናው በሙክራ እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ #በራሱ_መምህር አማካኝነት በበለጸገው ሥርዓት አማካኝነት ነው።

የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ የዛሬው ተግባት እጅግ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

የዚህን ትምህርት ቤት ተሞክሮ ወደ ሌሎች በዞን ወደሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአጭር ጊዜ ለማስፋፋት እንደሚሰራ ገልጿል።

ይህ የኦንላይን (Online) ፈተና ዝግጅት ከማዳበር ባሻገር ለተማሪዎች የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና እንድያጎለብቱ መልካም እድል መሆኑን ትምህርት ቤቱ አሳውቋል።

ትምህርት ቤቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ዉጤታማ ለመሆን እየጣራ መሆኑን አመልክቷል።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
8.6K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 23:02:01


“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ 'ተቋም' እንደሌለ የትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን አሳውቋል።

የትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መቋቋም የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 እንዲሁም በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 መሰረት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል መጠሪያ ግንቦት 29/2014 ዓ.ም እንደተቋቋመ በመግልጽ በማህበራዊ ድረ-ገጽ እየተዋወቀ የሚገኝው "ተቋም" እውቅና የሌለው መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በማለት ራሱን እያስተዋወቀ የሚገኘው "ተቋም"፤ ከባለሥልጣኑ ምንም አይነት ፈቃድ ያልተሰጠው እንደሆነ ተመላክቷል።

በቀጣይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ ባለስልጣኑ አሳውቋል።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝
7.2K viewsedited  20:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ