Get Mystery Box with random crypto!

የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በ ' ቴሌ ብር ' መክፈል ሊጀመር ነው ገንዘብ ሚኒስቴር ፤ በባንኮ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በ " ቴሌ ብር " መክፈል ሊጀመር ነው
ገንዘብ ሚኒስቴር ፤ በባንኮች በኩል ተከፋይ የሚሆነውን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ወደ " ቴሌ ብር " የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ለማሸጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕ/ተ/ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህ ይፋ የሆነው።

አቶ አህመድ ሽዴ ምንድነው ያሉት ?

" አሁን በባንኮች የክፍያ ሥርዓት በጥቅል (በበልክ) እየተከፈለ ያለውን ሒደት በቀጣይ ወደ ቴሌ ብር ለማሸጋገር ሥራዎች እየተሠሩ ነው። "

ይህ በተመለከተ ' ኢትዮ ቴሌኮም ' ምን አለ ?

ቺፍ ኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ፦

" በመንግሥት የተያዙት ጉዳዮች ወቅቱን ጠብቀው ቢገለጹ ይሻላል።

ነገር ግን ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ዝግጅትና አቅም አለው።

ተቋሙ በሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎቱ እስካሁን ከ32 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን አገልግሎት እየሰጠ እንደገሚገኘው መጠን የተዘረጋው ሲስተም አገልግሎቱን በቀላሉ ለመስጠት ያስችለዋል።

የትኛውም ውሳኔ ከሚመለከተው አካል ከመጣ መሥራት ይቻል።

ደመወዝ በቴሌ ብር መከፈሉ የተቋማትን ቅልጥፍና ለመጨመር አስተዋጽኦ ያድረጋል።

በዕረፍትና በበዓላት ወቅት የሚውል የደመወዝ ክፍያ ቀንና ተዛማጅ ጉዳዮች ለደመወዝ ከፋዩም ሆነ ተከፋዩ በሚያመች ለመክፈል ያስችላል።

እስካሁን ባለው አገልግሎቱ እንደ ደመወዝ ዓይነት የጅምላ (በበልክ) ክፍያ በሚከፈልበት ወቅት ሠራተኞች የደመወዛቸውን እስከ 35 በመቶ ያለምንም ዋስትና መበደር ይችላሉ። በቀጣይ ሌሎች ተጨማሪ አማራጮችም ይቀርባሉ።
እስካሁን ድረስ ግን ከሚመለከተው አካል የመጣ አቅጣጫ የለም። " ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊ ደመወዥ በ " ቴሌ ብር " ለማድረግ ስለታሰበው እቅድ በተመለከተ " እንዲህ መባሉን መረጃ የለኝም " ብለዋል።

በባንኩ በኩል የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ የሚከፍል መሆኑን የገለፁት እኚሁ ኃላፊ ለዚህ አገልግሎቱ ምንም ዓይነት ክፍያ የማይጠይቅበት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በቴሌ ብር በኩል ደመወዝ ይከፈል ከተባለ ግን አሁንም ኢትዮ ቴሌኮም የሚጠቀመው ከባንኮች ጋር በመተሳሰር መሆኑ አይቀርም ብለዋል፡፡

አጫጭር መረጃ ፦

እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ፦

- የመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ድርሻን ለማሳደግና እስካሁን የ159 ባለ በጀት መ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ዘዴ እንዲተገብሩ ተደርገዋል።

- በተያዘው ዓመት የዘጠኝ ወራት 79.2 ቢሊዮን ብር ክፍያ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ተከፍሏል።

- ኢትዮ ቴሌኮም የመንግሥት የኤክትሮኒክስ ክፍያ ድርሻ ለመወጣት እንዲያስችለው የሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ ነው የታክስ ክፍያ አሰባሰብም ሥርዓቱ በቴሌ ብር እንዲከፈል የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቷል።

እንደ ኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ፦

- የቴሌ ብር የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ እስከ የግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ 32.2 ሚሊዮን ደንበኞች አፍርቷል።

- እስካሁን ከ375.2 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ግብይቶች (ትራንዛክሽንስ) ተፈፅሟል።

- የነዳጅ ክፍያ በአስገዳጅነት በዲጂታል እንዲፈጸም ከተደረገበት ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ 2.7 ቢሊዮን ብር ግብይት ተፈፅሟል።
ሪፖርተር ጋዜጣ
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA