Get Mystery Box with random crypto!

ድሬዳዋ በድሬዳዋ የተስተዋለውን ከፍተኛ የሙቀት ተከትሎ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የጥንቃቄ መልዕክት | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ድሬዳዋ
በድሬዳዋ የተስተዋለውን ከፍተኛ የሙቀት ተከትሎ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፈ
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን መስተዋሉን አስመልክቶ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለነዋሪዎች የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፏል።

ቢሮው በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው(ከፍተኛ ደም ግፊት፣የስኳር ህመም፣የልብ ህመም፣የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአይምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ ከታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ፤

2. እቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ፤

3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት፤

4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ፤

5. አመጋገብዎን ማስተካከል(ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)፤

6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት፤

7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ፤

8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው፤

9.የተለያየ ህመም  ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ማድረግ፣ የታዘዘውን መድኃኒት በትዕዛዙ መሰረት በመውሰድ ጤናዎን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA