Get Mystery Box with random crypto!

በፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተፈፃሚነት የሚቆጣጠርና የሚያረጋግጠው ልኡክ ወይንም (ኤዩ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

በፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተፈፃሚነት የሚቆጣጠርና የሚያረጋግጠው ልኡክ ወይንም (ኤዩ ኤም ቪሲኤም) ለሁለት ቀናት በመቀሌ ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫው የትግራይን መከላከያ ሀይል ወይንም ቲዲኤፍ ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ወሳኝ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ግጭት አስተዳደር ዳይሬክተር አልሀጂ ሳርጆህ ባህ እንደተናገሩት ሁሉም አካላት በበጎ ፈቃደኛነት በመሳተፋቸውና ሰላም ወዳዱ ህዝብ በመተባበሩ የተነሳ ጥሩ ውጤት ሊገኝ ተችሏል፡፡

እስከ ሰማኒያ አምስት ፐርሰንት የሚሆነውን ከባድ መሳሪያ ትጥቅ ለማስፈታት መቻሉንም አስረድተዋል፡፡ ቀጣዩ እርምጃ የሚሆነው ቀላል መሳሪያዎችን ማስፈታት፣ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማምከንና የቀድሞ ታጣቂዎችን ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የልኡካን ቡድኑ ሀላፊ ሜጀር ጄኔራል ስቴፈን ራዲና በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በመቀሌ ከባድ መሳሪያዎና የአየር መቃወሚያዎች ትጥቅ ሲፈታ ለመመልከት ችለናል፡፡›› ያሉ ሲሆን የሞርታርና ፀረ ታንክ መሳሪያዎች መፍታቱ ሂደት በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚጠናቀው ገልፀዋል፡፡ በሚቀጥለው ወር ወደሁመራ የመሄድ እቅድ እንዳላቸው ያስታወቁት ሜጀር ጄኔራሉ አክሱምና ሽሬን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የጦርነት ቅሪቶችን የማፅዳት ስራ እንደሚቀርም አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህ ልኡክ እንደልቡ በትግራይ ክልል እንዳይንቀሳቀስ የኤርትራ ወታደሮች እንቅፋት እንደፈጠሩበት ገልጿል፡፡ የኤርትራ ወታደሮች የተቆጣጠሩት የትግራይ ክፍል እንዳለ የጠቆመው ጌታቸው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለቆ እንዲወጣ ግፊት እንዲያደርግም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA