Get Mystery Box with random crypto!

ጥንቃቄ በጌታቸው ሺፈራው የተፃፈ!! አሸባሪው  ትህነግ በተለያዩ ግንባሮች መመታቱን ተከትሎ አ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ጥንቃቄ

በጌታቸው ሺፈራው የተፃፈ!!

አሸባሪው  ትህነግ በተለያዩ ግንባሮች መመታቱን ተከትሎ አብረውት የሚሰሩት የኦነግ ፅንፈኞች ኦሮሚያ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለመፈፀም አበክረው እየሰሩ ነው። ኦሮሚያ ውስጥ ፋኖ በሌለበት በየቀኑ ፋኖ ኦሮሞን ያጠቃ በማስመሰል ዜናዎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ የቲውተር ዘመቻዎችን በየቀኑ እያደረጉ ነው። በተለይ በቅርብ ቀናት ውስጥ ትህነግ እየተመታ መሆኑን ሲያውቁ አንዴ የአማራ ኃይል፣ ሌላ ጊዜ የአማራ ሚሊሻ፣ በአብዛኛው ፋኖ እያሉ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው። ለአብነት ያህል ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ እንኳን በየቀኑ ከሁለት ሶስት ጊዜ በላይ መሰል ፕሮግራሞችን ሰርተዋል። ቲቪያቸው ውሎውን እነዚህን ፕሮግራሞች ማስተላለፍ ሆኗል።

በሰሜን አጋራቸው የተመታባቸው እነዚህ ፅንፈኞች ኦሮሚያ ውስጥ ጭፍጨፋ በመፈፀም፣ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በተጋቱት የሀሰት ትርክት በሚጠሉት ህዝብ ላይ  በቀላቸውን መወጣት፣ አጋራቸውን ለመዳን ኃይል መበተን ላይም ጭምር እየሰሩ ነው። ኦነግ ሸኔ የገደላቸውን ንፁሃን በሌለበት ፋኖ የገደላቸው በማስመሰል ጭፍጨፋና ግጭት እንዲፈጠር እየሰሩ ነው።

የሚያገባቸው አካላት ሁሉ የኦነግ ፅንፈኞች ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንዲፈፀም እየሰሩበት ያለውን መንገድ በመገንዘብ ከአሁኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።

የዩቲዩብ ቻናላችንን ጎብኙልን ሰብስክራይብ አድርጉን

https://youtube.com/channel/UCw9EUpuNrwP0hLvdmXz-ZBQ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA