Get Mystery Box with random crypto!

የዘንድሮው የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ አሸናፊ ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድላቸው የጠበበ ነው ተ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የዘንድሮው የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ አሸናፊ ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድላቸው የጠበበ ነው ተባለ

የ2022 ኢትዮጵያዊያን የድቪ እድለኞች ለአል ዓይን እንዳሉት አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ በተገቢው መንገድ እያስተናገደን አይደለም ብለዋል። የአሜሪካና ኢትዮጵያ ወቅታዊ ግንኙነት የድቪ እድለኞችን እየጎዳ መሆኑ እድለኞቹ ተናግረዋል።

በአሜሪካ ድቪ ሎተሪ አሰራር መሰረት እድል እንደወጣልን ግንቦት ሰባት 2021 ላይ አወቅን የሚሉት እነዚህ ግለሰቦች የቪዛ ፕሮሰሳችን እስከ መስከረም 30 ቀን 2022 ባሉት ጊዜያት ውስጥ ማለቅ ቢኖርበትም እስካሁን ኢምባሲው አልጠራንም ብለዋል።

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ ለዓል አይን በሰጠው ምላሽ " የድቪ ሎተሪ እድለኛ ተሆነ ማለት ቪዛ ይገኛል፣ ለቪዛ ቃለመጠይቅ ይጠራል ወይም ቪዛ ይሰጣል ማለት አይደለም" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።


@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA