Get Mystery Box with random crypto!

የቅዱስ ዮሴፍ እና የአሳይ ት/ቤት ግቢ ጉባኤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ estifanosgubae — የቅዱስ ዮሴፍ እና የአሳይ ት/ቤት ግቢ ጉባኤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ estifanosgubae — የቅዱስ ዮሴፍ እና የአሳይ ት/ቤት ግቢ ጉባኤ
የሰርጥ አድራሻ: @estifanosgubae
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 239
የሰርጥ መግለጫ

የቅዱስ ዮሴፍ እና አሳይ ትምህርት ቤት ግቢ ጉባዔ ኦፊሻል ቴሌግራም ቻናል፡፡
ተቀላቅለው አብረን የእግዚአብሔርን ቃል እንማር፡፡

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 21:26:28 ምጽዋት የፊት መብራት ናት

"ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ ከምጽዋት በላይ ታላቅ ነገር እንደሌለ ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከነበረበት የበደል ዕዳ የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና!"

#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ


❖.... ....❖ ❖.... ....❖
☞ @L
https://t.me/Betekereseteyane

v
37 viewsSasash, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:49:18 እንኳን አደረሳችሁ!!!
ሰኔ 30 የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ልደቱ
ነው

በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው፤ ሐዋርያው፤ ነብዩ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ቀኑ ነው፤ መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ነው ሚያዚያ 15 እረፍቱ ነው፤ አንገቱ ከተቆረጠ በኋላ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ ለ15 ዓመት በሳውዲ አረቢያና አካባቢው ወንጌልን ሰብካለች፤ የካቲት 30 ቀን የዮሐንስ ራስ የተገለጸችበት ቀን ነው። ከነዚህ አራት በዓላት ሁለቱን ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉን አውጥታ በደማቁ ታከብረዋለች እነዚህም ሰኔ 30 ልደቱና መስከረም ሁለት አንገቱ የተቆረጠበትን ቀን ነው።

ጨካኝ ሄሮድስ የቤተልሔም ህጻናትን ሲጨፈጭፍ መጥምቁ ዮሐንስ ከእናቱ ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር ወደ ሲና በርሃ ተሰደደ፤ ኤልሳቤጥ በጣም አርጅታ ነበር ያን በረሃ ታዲያ እንዴት ቻለችው ያውም ልጅ አዝላ ልጅ ተሸክማ ረዳት ሳይኖራት ብቻዋን፤ አባቱ ዘካርያስ በምኩራብ በመሰዊያው ፊት ልጅህን አምጣ ብለው አንገቱን ቆርጠው ገደሉት። ኤልሳቤጥም ሲና በርሃ ላይ ሞተች ህጻኑ ዮሐንስ ብቻውን ቀረ፤ የእናቱን በድነ ስጋ አቅፎ አለቀሰ፤ሁሉን ቻይ ሁሉን የሚያይ፤ ሁሉን የሚመረምር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን እናቴ ሆይ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በበርሃ አርፋለች እንቀብራት ዘንድ እንሂድ አላት ደመና ጠቅሰው ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትለው ሄደዋል ገንዘውም ቀብረዋታል፤ ከዚህ በኋላ እመቤታችን ልጄ ወዳጄ ሆይ ዮሐንስን ይዘነው እንሂድ አለችው የለም እናቴ፤ እርሱ እዚው ይቆያል መንገዴን ጠራጊ ነው፤ ኑሮው በዚሁ በርሃ ነው፤ ጊዜው ሲደርስ ወደ ዮርዳኖስ ይመጣል ያጠምቀኝማል ያኔ አንድነቴ ሶስትነቴ ይገለጣል አላት፤ ትተውት ተመለሱ።

ከመሞቷ በፊት እናቱ ያሰፋችለትን የግመል ቆዳ አገልድሞ አንቦጣ የሚባል ቅጠልና የበርሃ ማር እየበላ በበርሃ ኖረ 30 ዓመት ከ 6 ወር ሲሆነው፤ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ” እያለ ከበርሃ ወጣ ሉቃ 3፥3። "እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤" ማቴ 11፥11። ይህ የጌታችን ምስክርነት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
44 viewsSasash, 06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:02:45 ስትኖር ለብቻህ አትኑር

የሌሎችን ችግር በመፍታት ኑር
ገንዘብ ካለህ በገንዘብህ ደሃውን በመርዳት ኑር
ጉልበት ካለህ በጉልበትህ ደካመውን በመርዳት ኑር
እውቀት ካለህ እውቀትህን ሌላው በማካፈል ኑር
ሥልጣን ካለህ ለተበደሉት በመፍረድ ኑር
ቤት ካለህ ጎዳና ላይ ወድቆ የሚያድረውን ወንድምህን
በማስጠጋት ኑር
ልብስ ካለህ ራቁቱን ላለው ወንድምህ በማልበስ ኑር
ምግብ ካለህ የሚበለው ላጣው ወንድምህ በማብላት ኑር
ገንዘብ ካለህ ለሌላው አካፍል የአንተ ገንዘብ ባንክ
ተጨናንቆ ደሃ ሲቸገር እግዚአብሔር ይታዘብሃል
ጠንካራ ጉልበት እያለህ ደካማውን ወንድምህን ሳትረዳ
ስትቀር ጉልበት የሰጠህ አምላክህ ይመለከትሃል ጠንካራው
ጉልበትህ ደካማ ይሆናል አንተም በጊዜህ አንሱኝ ጣሉኝ
ትላለህ የአንተ ጠንካራ ጉልበት ደካማውን ለማሸነፍ አይደለም
የተፈጠረው ደሃውን ለመርዳት ነው እንጂ
እውቀትህ ሌላ ካላስተማርክበት እውቀቱን የሰጠህ ፈጣሪህ
እውቀትህን እንደሚነሳህ አስብ እውቀት ችግር መፍቻ ነው እንጂ
ችግር ማምጫ አይደለም እውቀት ወደብርሃን የሚመራ እንጂ
ወደጨለማ የሚወስድ አይደለም የአንተ እውቀት የዶክትሪት
የማስትሪት የድግሪ የዲፕሎማ የመጽሐፍ የቅኔ የድጓ የአቋቋም
የዝማሬ የቅዳሴ እውቀትህ ላላወቁት ለማሳወቅ እንጂ
ለመወደስ ለመከበር ለመፈራት አይደለም
በስልጣንህ የምታዳላ ከሆነ ሰማያዊ ስልጣን ባለው
ፊት ተከሰህ ስትቀርብ መልስ ታጣለህ ስልጣንህ ለተበደለ
ፈራጂ ለተቀማ አስመላሽ የድኀ እንባ አባሽ መሆን አለበት ዛሬ
ሰዎች ተከሰው ወደአንተ ፊት እንደቀረቡ ሁሉ አንተም ተከሰህ
በፈጣሪህ ፊት ትቀርባለህና
ልብስህ ቁም ሳጥን ሞልቶ ሻንጣ አጨናንቆ አንተ በሰላሳ
ቀን ሰላሳ ልብስ እየቀየርህ እንዳንተ ገላ ያለው ሰው ራቁቱን
ሁኖ ብርድና ሙቀት ሲፈራረቅበት የማታለብሰው ከሆነ ሰማይን
በደመና የሚያለብሰው ምድርን በእሳር የሚሸፍነው አምላክህ
ያዝንብሃል
አንተ ምን ልብላ ብለህ አማርጠህ ትበላለህ በቀን አራት
አምስት ጊዜ ትበላለህ እንዳንተ ምግብ የሚፈልገው ወንድምህ
የሚበለው አጥቶ ሲራብ ትተኸው ስትበላ በዝናብ አብቅሎ
በፀሐይ አብስሎ የሚመግብህ አምላክ የሰጠህን ምግብ
ይነሰሃል ታመህ ያየሀውን ሁሉ እንዳትበላ ያደርግሃል
ስትቆርጠው የነበረው ጮማ ስትጎነጨው የነበረው ውስኪ ሁሉ
ይቀራል
ገንዘብህ በባንክ እየደለበ ሌላውን ካረዳህበት ስትሞት
አብሮህ አይቀበርም ወደመቃብር ስትወርድ በአንድ ነጭ ነጠላ
ተጠቅልለህ ነው ሀብትህ ሁሉ አይከተልህም እግዚአብሔር
ሀብት የሰጠህ አንተ ለዳሀው ሰጥተህ እንድትጸድቅ ዳሀው
ተቀብሎ እግዚአብሔርን እንዲአመሰግን ነው
ሰው ሆይ በትክክለኛው መንገድ ኑር
ለኳስ ሁለት ሰአት ጊዜ ሰጥተህ ለቅዳሴ አንድ ሰአት
አልሰጠህም
ለፊልም ረጅም ጊዜ ሰጥተህ ለወንጌል አጭር ጊዜ አጥተሃል
ለኳስ ጨዋታ ተወራርደህ ብር ትሰጣለህ ለቤተ ክርስቲያን
ማሰሪያ እጅህ ይታሰራል
ለፊልም እስፖንሰር ትሆናለህ ለወንጌል ግን አምስት ሳንቲም
ለማውጣት ትቆረቆራለህ
የፊል አክተሮችን አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ የኳስ ኮከቦችን
በደረጃ ትጠራቸዋለህ
ወንጌሉን የጻፉት አነማናቸው ስትባል መልስ ታጣለህ
ሰው ሆይ አንተ ለዘለዓለም በምድር አትኖርም በሰማይ ለመኖር
የተፈጠርህ ነህ ወደምድር ያወረደህ የአባትህ የአዳም የናትህ
የሄዋን ኀጢአት ነው እንጂ ሀገርህ በሰማይ ነው ለተወሰነ ጊዜ
በምድር ትቆያለህ ሇላ ከምድር ወደላይ ትወሰዳለህ
በሰማይ በበጎ ቦታ ለመኖር በምድር ሳለህ መልካም ስራ ስራ
ከጎንህ የምታውቀው ሰው ሲሞት ከማልቀስ ባሿገር ነገ አንተ
እነደምትሞት ተማርበት ጎረቤትህ ዛሬ ሲሞት ነገ ተረው የአንተ
መሆኑን አትርሳ
ዓለም ጨለማ ናት ወደጨለማ ሳትወስድህ ወደብርሃን ተጉዘህ
ቅደማት የምታልፈው ዓለም እድሜህን በከንቱ ሳትጨርስብህ
ማለፏን አውቀህ ቅደማት ዓለም የዛሬ ናት ዛሬ አስደስታ ነገ
ታስለቅስሃለች
ዛሬ አሳይታ ነገ ታሳጣሀለች
ዛሬ አጥግባ ነገ ታስርብሐለች
ዛሬ ሹማ ነገ ትሽርሃለች
ዛሬ አክብራ ነገ ታዋርድሃለች
ዛሬ አሳምራ ነገ ታጠቁርሐለች
ዛሬ አድንቃ ነገ ትንቅሃለች
ዛሬ አጨብጭባለህ ነገ ድንጋይ ትወረውርብሐለች
ዛሬ ከፍ ከፍ አድርጋ ነገ ዝቅ ዝቅ ታረግሃለች
ለአንተ አባቶች አልሆነችም መቃብር ከታቸዋለች ከቀደሙት
አባቶችህ ተማር አባትህ የት? አለ መቃብር ውስጥ አይደል
እናትህ የት ?አለች መቃብር ውስስጥ አይደል የምታውቃቸው
ካንተ ቀድመው የነበሩ ዝነኞች ባለ ሀብቶች አርቲስቶች
የሃይማኖት አባቶች ባለ ስልጣናት ሁሉ መቃብር ውስጥ
እንደሆኑ ተረዳ
ስማቸው ከመቃብር በላይ ቀርቷል መልካም የሰሩት በመልካም
ስም ክፉ የት በክፉ ስም ይታወሳሉ
ሰው ሆይ ለሰው ችግር ሳትሆን ሰውን በመርዳት ኑር::
47 viewsSasash, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:45:09 #ክብሬ_ነው

ክብሬ ነው ክብርህን መናገሬ
ፅድቄ ነው ፍቅርህ መመስከሬ
ጌታዬ አምላኬ እልሃለሁ (2)
ስጠራህ ሳመልክህ እኖራለሁ (2)
#አዝ
አይቼ የእጅህን ታምራት
ሰምቼ የቃልህን ትምርት
ሆኛለሁ ምስክር ላዳኝነትህ
ስጋን ተዋህደህ ለኛ መገለጥህ (2)
#አዝ
ተከተልኩ ሁሉን ነገር ንቄ
መድኃኒት መሆንክን አውቄ
ከመልካሟ ቤትህ ተጠልያለሁ
የእጅህን በረከት ካንተ እጠግባለሁ (2)
#አዝ
እርፍ ይዤ ላላርስ ወደኅውላ
እያየው መረቤን ስትሞላ
እመካብሃለሁ ባንተ መድህኔ
አምላኬ ነህና የምትራራ ለኔ
አባቴ ነህና የምታስብ ለኔ
#አዝ
ቸርነት ምረት ከበዛልኝ
ለስምህ ውዳሴ ቅኔ አለኝ
ክብሬና ሞገሴ አንተ ነህ ጌታ
ተመስገን (2) ጠዋትና ማታ (2)

በቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ
92 viewsSasash, edited  04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:33:11
54 viewsSasash, 04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:33:11
53 viewsSasash, 04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 10:17:45 በሰፈርከው ልክ ነው የምትመዘነው።

አንድ ቅቤ አምራች ገበሬና ዳቦ አምራች ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡ በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡ ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት ተስማሙ፡፡

በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነጋዴ የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሄዱን አየ፡፡ በመጨረሻም ሚዛን ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም፡፡ ገበሬውንም አስጠራው፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ ‹ከተስማማነው
ውጭ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው?› ሲል
ጠየቀው፡፡ ገበሬውም ‹እኔ ፈጽሞ አልቀነስኩትም› ሲል በአግራሞት መለሰ፡፡ ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው፡፡ 150 ግራም ነው፡፡ ገበሬውም አዘነ፡፡ ‹እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም መለኪያ የለኝም፡፡ አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሐን ላይ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ቅቤውን በሌላኛው ሚዛን
አስቀምጠዋለሁ፡፡ ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ እልክልሃለሁ› አለው፡፡ ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው፡፡ ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው፡፡ ነጋዴው አፈረ፡፡ ‹የምታገኘው ለሌላው ባደረግከው ልክ ነው፡፡ 150 ሰጥተህ 300 ልታገኝ አትችልም፤ እባብ ሰጥተህ ርግብ፣
ድንጋይ ሰጥተህ ዳቦ፣ እሬት ሰጥተህ ማር ልታገኝ
አትችልም፤ አንተ ብቻ ብልጥ ልትሆን አትችልም፤ ማሾውን አጥፍተህ ብርሃን ልታገኝ አትችልም፤ ሌላው ገድለህ አንተ በሰላም ልትኖር አትችልም› አለው ገበሬው፡፡

ማንኛውም ድርጊት ተመሳሳይና ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ አለው፡፡ አንተ እዚህ ለብቻህ ቤትህ ውስጥ ሆነህ ክፉ ስታደርግ ሌላውም በቤቱ ብቻውን ሆኖ ክፉውን ይመልስሃል፡፡ ‹እዛም ቤት እሳት አለ› እንዳሉት ነው አለቃ ገብረ ሐና፡፡ አንተ ጎመድ ይዘህ ከወጣህ ሌላውም አያቅተውም፤ አንተ ገጀራህን ከሳልክ ሌላውም ይስላል፤ አንተ የሌላውን ወገን ስታፈናቅል፣ ያኛውም ያንተን ወገን ያፈናቅላል፡፡ ዛፍ ቆርጠህ ዝናብ፣ በካይ ጋዝ እየለቀቅክ የተስተካከለ የአየር ንብረት አትጠብቅ፡፡ ተፈጥሮም በሰጠሃት መጠን ነው የምትመልስህ፡፡ በዓለም ላይ ሚዛኑ አንድ ነው፤ ተመዛኞቹ ግን ይለያያሉ፡፡ እዚህ ካጎደልክ፣ እዚያም ያጎድሉብሃል፡፡ እዚህኛው ዩኒቨርሲቲ የዚያኛው ልጅ አለ፤ እዚያኛው ዩኒቨርሲቲም የአንተ ልጅ ይገኛል፡፡ እዚህ የአንተ ወገን ብዙኃኑን ይዟል፣ እዚያ ግን አናሳ ነው፡፡ እዚህ አናሳ የሆነው ደግሞ እዚያ ብዙ ይሆናል። የብዙኃን ወገን በሆንክበት ቦታ አናሳውን ካሰቃየህ፣ አናሳ በሆንክበት ቦታ ደግሞ ብዙኃን ያሰቃዩሃል፡፡ እዚህ ባለ ሥልጣን እንደሆንከው እዚያ ተራ ትሆናልህ፡፡ የሚያዋጣው በሚዛኑ ልክ ትክክለኛውን ማድረግ ብቻ ነው፡፡ሰላም ለሀገራችን ሰላም ለሁላችን።

ዲ/ን ኤርምያስ
68 viewsSasash, 07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 18:57:12 #ትሕትና

በትክክል ትሑት የኾነ ሰው ማን እንደ ኾነ ማወቅ ትወድዳለህን? በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት የነበረውን ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ መምህረ ዓለም፣ መንፈሳዊ አንደበተ ርቱዕ፣ ንዋይ ኅሩይ፣ ወጀብ የሌለበት ወደብ፣ የማይናወጽ ግንብ፣ በአካለ ሥጋ ትንሽ ሲኾን አክናፍ እንደ ተሰጡት ኾኖ ምድርን ኹሉ ያካለለውን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ ያልተማረው ግን ደግሞ የተራቀቀውን፣ ድኻ ግን ደግሞ ባለጠጋ የኾነውን ይህን ቅዱስ ሰው ተመልከት፡፡ እልፍ ጊዜ መከራዎችን የተቀበለው፣ አእላፋት ጊዜ ዲያብሎስን ድል የነሣው፣ “ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም፤ ከኹላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ” ብሎ የተናገረው ተወዳጅ ጳውሎስን በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (1ኛ ቆሮ.15፡10)፡፡ ብዙ ጊዜ መታሰርን፣ ብዙ ጊዜ መገረፍን፣ ብዙ ጊዜ በድንጋይ መወገርን፣ [ከበረኻ አራዊት ጋር መጋደልን፣ በባሕር ውስጥ ለሦስት ቀናት ሲዋኝ ውሎ ሲዋኝ ማደርን፣ ቀንና ሌሊት ብዙ ጦምን፣ በብርድና በራቁትነት መኾንን] የታገሠ የተቀበለ፣ በመልእክታቱ ዓለምን በወንጌል መረብነት ያጠመደ፣ ከሰማያት በመጣ ሰማያዊ ቃል የተጠራው እርሱ ራሱን ዝቅ አድርጎ፡- “እኔ ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ ነኝ” ያለውን ብፁዕ ጳውሎስ አማን በአማን ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (2ኛ ቆሮ.11፡23-27)፡፡

እንግዲህ የቅዱስ ጳውሎስን የትሕትናው ታላቅነት ታያለህን? ራሱን ዝቅ አድርጎ ታናሽ ነኝ ሲል ትመለከታለህን? “እኔ” አለ ቅዱስ ጳውሎስ፥ “ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ፤ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ፡፡” በትክክል ትሕትና ማለት ይህ ነው - በኹሉም ረገድ ራስን ዝቅ ማድረግ! ራስን እንደ ታናሽ መቊጠር! እነዚህን ኃይላተ ቃላት የተናገራቸው ማን እንደ ኾነ በነቂሐ ልቡና በሰቂለ ሕሊና ኾነህ አድምጥ! የሰማይ ሰው የምድር መልአክ የሚኾን ጳውሎስ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ዓምድ የሚኾን ጳውሎስ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን እጅግ አብልጬ የምወደውም ለዚህ ነው፡፡ ምግባር ትሩፋት ሥጋ ለብሳ ሥግው ኾና ተውባ ተሞሻሽራ የማያት በእርሱ በብፁዕ ጳውሎስ ዘንድ ነውና፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ፊት በዓይነ ሕሊናዬ ተቀርፆ የሚሰጠኝን ተድላ ደስታ ያህል የብርሃን ጮራዋን የምትለግሰው ፀሐይ ለዓይኖቼ ደስታን አትሰጠኝም፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ፀሐይ የሥጋ ዓይኖቼ በብርሃን እንዲያዩ ታደርጋቸዋለች፤ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ ግን ዓይነ ልቡናዬ አክናፍ ኑሮት ወደ ሰማየ ሰማያት እንድወጣ ያደርግልኛል፡፡ ነፍስን ከፀሕይ ይልቅ ጽድልት፣ ከጨረቃም ይልቅ ልዕልት እንድትኾን ያደርጋል፡፡ የምግባር የትሩፋት ኃይሏ ሥልጣኗ ይህን ያህል ነውና - ሰውን መልአክ ታደርገዋለች ፡፡ ነፍስ አክናፍ አውጥታ ወደ ሰማየ ሰማያት እንድትበር ታደርጋለች፡፡ ተወዳጅ ጳውሎስም የሚያስተምረን ይህንን ነው - ምግባርን ! ስለዚህ ነቅተን ተግተን በምግባሩ አብነት እናደርገው፤ እርሱን እንምሰል፡፡

#ንስሓና_ምጽዋት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው
81 viewsSasash, 15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 09:25:27 ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
86 viewsSasash, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:49:44
91 viewsSasash, 06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ