#ክብሬ_ነው ክብሬ ነው ክብርህን መናገሬ ፅድቄ ነው ፍቅርህ መመስከሬ ጌታዬ አምላኬ እልሃለሁ (2) ስጠራህ ሳመልክህ እኖራለሁ (2) #አዝ አይቼ የእጅህን ታምራት ሰምቼ የቃልህን ትምርት ሆኛለሁ ምስክር ላዳኝነትህ ስጋን ተዋህደህ ለኛ መገለጥህ (2) #አዝ ተከተልኩ ሁሉን ነገር ንቄ መድኃኒት መሆንክን አውቄ ከመልካሟ ቤትህ ተጠልያለሁ የእጅህን በረከት ካንተ እጠግባለሁ (2) #አዝ እርፍ ይዤ ላላርስ ወደኅውላ እያየው መረቤን ስትሞላ እመካብሃለሁ ባንተ መድህኔ አምላኬ ነህና የምትራራ ለኔ አባቴ ነህና የምታስብ ለኔ #አዝ ቸርነት ምረት ከበዛልኝ ለስምህ ውዳሴ ቅኔ አለኝ ክብሬና ሞገሴ አንተ ነህ ጌታ ተመስገን (2) ጠዋትና ማታ (2) በቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ 92 viewsSasash, edited 04:45