Get Mystery Box with random crypto!

ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamic_page_musab99 — ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page
የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamic_page_musab99 — ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page
የሰርጥ አድራሻ: @eslamic_page_musab99
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.46K
የሰርጥ መግለጫ

👌ሁሌም ቢሆን ለዲንህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!
አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል።
👌ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።
«አላህ መልካም ነገርን የፈለገለት ሰው በዲን ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖረው ያደርገዋል።» ነቢዩﷺ
Please don't leave, tell us the mistake
#4_any comment & promo:- @Al_Musab99

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-09 12:31:25
صلى الله عليه وسلم
116 views ⓃⓔⓑⓊ , 09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 12:31:25 Quran
Qari- aldosry
Suretul Kahf

@Islamic_direction
115 views ⓃⓔⓑⓊ , 09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 12:31:25 ጁምዓ /  الجمعةِ

اللهم امين يارب العالمين

@Islamic_direction
132 views ⓃⓔⓑⓊ , 09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:48:58
የኔ አላህ

አል_ወሊይ የኔ አላህ ወዳጅ እንዲሁም ረዳታችን ነው።
አአንዳንዴ ስከፋ ብዙ አስብና ሙስሊም ስለሆንኩ አላህዬ ስለመረጠኝና ስለወደደኝ በመንገዱ እንድመላለስ ሰለፈቀደልኝ ሁሉንም እረሳና ከልቤ ደስስ ይለኛል ምክኒያቱም የኔ አላህ ስንትና ስንት ለፀሀይ እና ጨረቃ ለእሳት ለጣኦታት ለተለያዩ ግዑዝ ነገራቶች የሚሰግዱና የሚያጎበድዱ ብዙሀኖች ባሉባት በዚች ጠፊ አለም ለኔ ግን ከሀይማኖት ምርጡ እስልምናን ሸለመኝ እሱን መገዛትን ለሱ ብቻ መስገድን ወፈቀኝ ምንምእንኳ ተገቢዉን መገዛት ባልገዛውም የሚገባዉ ያክል ሱጁድ ባላደርግም እሱ ግን ሁሌም ይወደኛል

መመረጤ በራሱ ጮቤ ያስረግጠኛል ሳልጠይቀው እንዳውቀው የለፈቀደልኝ ስለሚወደኝ አይደል ? እንዴታ! መንገዱን ሳልስት እንድገናኘው ጠይቄውማ አያሳፍረኝም ደግሞም ሙስሊምነት በራሱ ትልቅ ፈድል'ኮ ነው?!
ለዛም ነው አፌን ሞልቼ የኔ_አላህ ወዳጄ ረዳቴም ነው የምለው የኔ አላህ ከሚገባን በላይ ይወደናል በቀጥተኛው መንገዱም ላይ ፀንተን እንድንቆይ በተገቢውም ሁኔታ እንድንገናኘው ይረዳናል ምክኒያቱም እርሱ የሚወደን + የሚረዳን አል_ወልይ ነውና።

مَن يَه‍ْدِ اللَّهُ فَه‍ُوَ الْمُه‍ْتَدِۖ وَمَن يُضْلِلْ فَلَن تَجِدَ لَهُ وَلِيًّا مُرْشِدًا

አላህ የሚያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ ነው። የሚያጠመውመ ሰው ለርሱ አቅኝን ረዳት አታገኝለትም።
[አል_ካህፍ 17/١٧]

@Islamic_direction
@Islamic_direction
206 views ⓃⓔⓑⓊ , 07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:48:58
ተውሂድ የሁለት ሀገር ስኬት!!
~ተውሂድን ማወቅ)ከቤተሰቦችህ/ከልጆችህ /ጀመር!!
➘➘➘➘➘
ሽርክን አስጠንቅቅ
الشيخ ابن رمزان اله‍اجرب حفظه الله ))
@Islamic_direction
136 views ⓃⓔⓑⓊ , 07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:48:58
ከተውሂድ ጥቅሞች ውስጥ

ሸኽ አብዱረህማን አስሰአድይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል

በአንድ ሰው ቀልብ ውስጥ ተውሂድ ሙሉ ሆኖ ከተገኘ አሏህ ለዚህ ሰው፦
ኢማን እሱ ዘንድ የተወደደ ያደርግለታል።
ኢማን በቀልቡ ያስውብለታል።
ክህደት፣ አመፅና ወንጀል እሱ ዘንድ የተጠሉ እንዲሆኑ ያደርግለታል።
ከነዛ ቅኑን መንገድ ከተመሩት ያደርገዋል።
القول السديد(٢٤)

@Islamic_direction
130 views ⓃⓔⓑⓊ , 07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:48:58 የሽርክ አይነቶች ስንት ናቸዉ??

ሽርክ ሁለት ክፍሎች አሉት

እነሱም ፦ትልቁ ሽርክ እና
ትንሹ ሽርክ በመባል ይታወቃሉ።

❶.ትልቁ ሽርክ

➱ትልቁ ሽርክ ከኢስላም የሚያስወጣ እና ባለቤቱ ወደ አላህ በተዉበት ሳይመለስ ከሞተ በእሳት ዉስጥ ዝንተ አለምእንዲዘወትር የሚያረግ ትልቅ ወንጀል ነዉ።
➲ይህም አምልኮት (ኢባዳ)ከአላህ ዉጭ ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት ነዉ።
ለምሳሌ፦
➢ለእከሌ ብሎ ዱዓ ማረግ
➢ለእከሌ ብሎ ማረድ
➢የሞተን ሰዉ ይጠቅመኛል ወይም ይጎዳኛል ብሎ ማመን
➢ፉጡራን በማይችሉት ነገር መለመን እና ድረሱልኝ ማለት ወ.ዘ.ተ......

❷ትንሹ ሽርክ

➱ትንሹ ሽርክ ከኢስላም ባያስወጣም ተዉሂድን ያጎላል፤ወደ ትልቁ ሽርክም ሊያደርስ ይችላል።

ይህ የሽርክ ክፍል በሁለት ይከፈላል እነሱም፦

⓵በንግግር እና በተግባርም ግልፅ የሆነዉ። ለምሳሌ፦ ➤ከአላህ ዉጭ በሆነን አካል መማል ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ብለዋል።

➫ከአላህ ዉጭ በሆነ አካል የማለ ሰዉ በእርግጥም ክዷል (አጋርቷል) ቲርዝይ ተግቦታል

➤አላህ እና እንትና (ስለ ፈለጉ)ነዉ እንዲህ የሆንኩት ብሎ ማለት።

ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ
<<ለነብዩ "አላህ እና አንተ ስለፈለጋችሁ ነዉ" ሲሏቸዉ፤ እንዲህ አሉ "ለአላህ ባላንጣ ታድርገኝ አለን? አላህ ስለፈቀደዉ ብቻ በል"።>>

⓶ድብቅ ሽርክ፦የትንሽ ሽርክ ክፍል ሲሆን ስራዎችን ለይዩልኝ እና ይስሙልኝ መከወን ነዉ።
ለምሳሌ ፦
➢የሰዎችን አድናቆት በመከጀል ሰደቃ መስጠት
➢ሰላትን ማሳመር ለይዉልኝ ብሎ
➢ቁርአን ቢቀሩ ድምፅን ማሳመር ወ.ዘ.ተ ......

ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ብለዋል።

➫በጣም ከምፈራላችሁ ነገር ትንሹ ሽርክ ነዉ። ትንሹ ሽርክ ምንድን ነዉ? ተብለዉ ሲጠየቁ "ሪያዕ(ይዩልኝ እና ይስሙልኝ)ነዉ" በማለት መለሱ። በዃሪ ዘግቦታል

ሁላችንም ከሁለቱም ሽርክ እንጠንቀቅ ሌሎችንም እናስታውስ

ተውሂድ የተፈጠርንበት አላማ ነው !!
ሁል ግዜም ተውሂድ ይቀድማል

@Islamic_direction
136 views ⓃⓔⓑⓊ , 07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 17:35:35
አላህ ይሰትረናል........ ከዚያም ወደ ራሱ ይጠራናል......... ከዚያም ይቅር ይለናል........... ይወደናል........ ከዚያም ወንጀላችንን ወደ መልካም ስራ ይቀይርልናል

ያ አላህ ቸርነትህ

#ፍፁም_ቸር

ጥራትና ምስጋና ይገባህ ንጉሴ

@Islamic_direction
313 views ⓃⓔⓑⓊ , 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 17:35:35
የኔ_አላህ

የኔ አላህ ይቅር ባይ ነው ይቅር ማለትንም ይወዳል የሰው ልጅ ሊጎዳን እንደማይችል ውስጡ ሲያውቅ ይቅር ሊለን ይችላል፤ የኔ አላህ ግን ቻይ ሆኖ፤ የፈለገውን ነገር ማድረግ እየቻለ ነው ይቅር የሚለን፤ መቅጣት እየቻለ የሚያልፈን ነው።
አል-አፉው ከባድ ሚዛን ያለው ስም ነው። በእርግጥ የአላህ ስሞች ሁሉ ውብ ናቸው ለእኔ ግን አል-አፉው ትልቅ ስፍራ አለው አስቡት! አል-አፉው እኮ ማለት ይቅር ባይ ማለት ብቻ አይደለም! ሀጢያቱ መጀመሪያውኑ እንዳልተፈፀመ አድርጎ ይቅር ማለት ቢሆን እንጂ ሀጢያቱን ከመማሩ ማጥፋቱ ከማጥፋቱም እንደፈፀምነው እራሱ እንዳናውቀው ማስረሳቱ ከዛም አልፎ ስራችንን መውደዱና መቀበሉ ከውዴታው በኃላ ሳንጠይቀው የሚያስደስተንን የሆነ ሀላል ስጦታ መስጠቱን በውስጡ ስለያዘ ይህንን ስም በጣም እንድወደው አድርጎኛል! ግን እኛኮ ያልነው ይቅር በለን ብቻ ነበር አይደል?አላህዬ ግን ጥበቡ ሰፊ ነዋ፤ ባህሪያቶቹ ከአዕምሮ በላይ ናቸው።

የኔ አላህ ከሰራኸው ወንጀል በላይ ወደሱ መዋደቅህን ይወደዋል፤ በውብ ስሞቹ እየጠራህ ምህረቱን እንድትለምነው ይፈልጋል፤ በአል-አፉው ስም ከልብህ ስትለምነው አላህ ከተቀበለው ወንጀልህን ያስረሳሃል፤ ከመጥፎ ስራ መዝገብ ላይም ያጠፋታል፤ ይጠርጋታል የውመል ቂያማ ስትመጣ እንዲህ ሰራህ ብሎ አያስታውስህም፤ አይጠይቅህምም! ያ አላህ!

ግን ይሄ ሁሉ ለምን አያስብልም? ጌታዬ ስለሚወድህ ባንተ መወደድም ስለሚፈልግ ነው ለሱ በምድር ላይ ትልቁ ፍጥረት ነህና ሊያዝንልህ ይፈልጋል፤ ወንጀልህን ጠርጎልህ ጀነቱ እንድትገባ ይጓጓል!

ይህ ነው እንግዲህ የኛ አላህ! በስሙ ለመኖር ዝግጁ?
وَيَعْفُ عَن كَثِيرٍ
ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡

ኢላሂ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትንም ትወዳለህና ይቅር በለን!

@Islamic_direction
242 views ⓃⓔⓑⓊ , 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 11:42:59
ያ አላህ

ልባችን በዱንያ ፍቅር ስትፈተን ባንተ ፍቅር ሙላልን
በዱንያ ጭንቀት ስንረበሽ ባንተ ማዉሳት አረጋጋልን
በጥፋት ላይ ስንወድቅ ተውበትክን አግራልን
ኢባዳችን ላይ ስንዳከም ካንተ የሆነ ቁዋን ስጠን


ያ ሙጂብ

ሁሉም ቦታ ሆነው አንተን ከሚፈሩት
በክፉም በደግ ከልብ ከሚያመሰግኑህ
በጠዋትም በማታ ስምህን ከሚያወድሱት
ኢማናቸዉ ላንተ ያላቸውን ፍቅርና ፍራቻ እለት ከእለት ከምትጨምርላቸው ሙህሲን ባሮህ አድርገን
የሰዎችን ስሜት ለመጠበቅ ብለው አንተን ከሚያሳዝኑት አታድርገን
የታመሙትን አሽርልን
የሞቱብንን ማርልን

ያ ረቡ ረህማ ሀይልም ሆነ ብልሀት ያንተ ነውና ጠየቅንህ በነዚያ በሚያማምሩ ላንተ የተገቡህ በሆኑት በ99ኙ ስሞችህ

በድአችሁ አትርሱኝ የናንተም ሀጃ ይፈፀማል
@Islamic_direction
265 views ⓃⓔⓑⓊ , 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ