2022-10-08 06:39:03
#Gambella
" የአካባቢው ማህበረሰብ በተቻለው አቅም እራሱን እንዲጠብቅ አደራ እንላለን " - የጋምቤላ ክልል መንግስት
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል፤ ኑዌር ዞን በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ሲገድሉ ፤ አንድ የ11 ዓመት ታዳጊ አፍነውን ወስደዋል።
የጋምቤላ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን እንዳሳወቀው በቀን 26/01/2015 ዓ/ም ከቀኑ 12 ሰዓት ገደማ ላይ በኑዌር ዞን ፤ በማኮይ ወረዳ በሎንጆክ ቀበሌ የሙርሌ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው 3 ሰዎችን ሲገድሉ፤ አንድ የ11 ዓመት ታዳጊ አፍነው ወስደዋል።
ይህ ድርጊት የተፈፀመበት ቦታ " ጎርፍ ካጠቃቸው " ቦታዎች አንዱ ሲሆን ህብረተሰቡን የማረጋጋት እና ታጣቂዎች ለመያዝ እየተሰራ መሆኑን ክልሉ አሳውቋል።
የክልሉ መንግስት ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ በተቻለው አቅም እራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጊዜ ድንበር ጥሰው እየገቡ በኑዌር ዞን እና አኝዋሃ ዞን በሰው ህይወት ላይ አደጋ ሲያደርሱ እና በርካታ ከብቶችንም ዘርፈው ሲወስዱ ቆይተዋል።
@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
1.2K viewsDagi, edited 03:39