Get Mystery Box with random crypto!

' ተማሪዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተርፈዋል ፤ ወላጆችም ተረጋጉ ' - የሲግሞ ወረዳ ዛሬ በ | 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ 🌿

" ተማሪዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተርፈዋል ፤ ወላጆችም ተረጋጉ " - የሲግሞ ወረዳ

ዛሬ በጅማ ዞን ፤ ከሲግሞ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ስጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ የትራፊክ አደጋ ደርሶ ነበር።

ነገር ግን ተማሪዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸውን የወረዳው አስተዳደር አሳውቋል።

የተማሪ ወላጆችም ይህንን በማወቅ እንዲረጋጉ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የሲግሞ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን / ሱልጣን ኢብራሂም / ነው።

በዚህ አጋጣሚ ወቅቱ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ከማድረስ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት በመኖሩ አስሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እና በእርጋታ እንዲያሽከረርክሩ በድጋሜ አደራ እንላለን።

@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv