Get Mystery Box with random crypto!

🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ 🌿

የቴሌግራም ቻናል አርማ esat_tv9 — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ 🌿
የቴሌግራም ቻናል አርማ esat_tv9 — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ 🌿
የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv9
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.61K
የሰርጥ መግለጫ

ፈጣን መረጃዎችን ከኛ ዘንዳ ያገኛሉ

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-31 18:34:27
የማምረት ተግባራቸው ተስተጓጉሎ የነበሩ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ማምረት ጀመሩ!

በጸጥታ ችግር ምክንያት የማምረት ተግባራቸውን የተስተጓጎለው የታጠቅ እና የሙገር ሲምንቶ ፋብሪካዎች ወደ ማምረት መመለሳቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

@Esat_tv9
@Esat_tv9
1.7K viewsDagi, edited  15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 18:29:18
መግለጫ!!

"የትግራይ ሕዝብ ሕወሐት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው

የመከላከያ ሰራዊቱ መሥዋዕትነት የታሰበውን ግብ እንዲያሳካ የትግራይ ሕዝብ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የመከላከያ ሠራዊቱን በመንከባከብ፣ ስንቅ በማቀበል፣ ስለተደበቁ ጀሌዎችና የጦር መሣሪያዎች መረጃ በመስጠት፣ መንገድ በመምራት እና አካባቢውን በመጠበቅ የትግራይ ሕዝብ ከሠራዊቱ ጋር ተሰልፏል። ለዚህም መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ያለው ቅንጅት ሕወሐትን አስደንግጦታል። በዚህም የተነሣ "ምስለኔዎች ሊያስተዳድሩህ እየመጡ ነው" የሚል ውዥንብር እየነዛ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕወሓት ጋር የታገለው የምስለኔ አስተዳደር እንዲቀር ነው። የምስለኔ አስተዳደርን በክልሎች ላይ እንደገና የዘረጋው ሕወሐት በመሆኑ።

የትግራይ ሕዝብ በራሱ ልጆች እንጂ በማንም ሊተዳደር አይገባም።

ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ይሄንን አይፈቅድም። ሕወሐትም ይሄንን ያውቃል። ይደብቃል እንጂ። በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ የሕወሐትን የምስለኔ ቴአትር፣ በምስለኔነት ለኖረው ለሕወሐት ትቶ፣ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ትብብር እንዲያጠናክር መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።"

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
@Esat_tv9
@Esat_tv9
1.8K viewsDagi, edited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 20:22:08 https://t.me/delalochu1
2.2K viewsDagi, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 07:31:41
"በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኞች ፍተሻ ሲደረግ የነበረው ብዙ ተማሪዎች ድልድዩ ላይ እንዲሰለፉ እና እንዲቆሙ ተደርገው ነው።" - የአይን እማኞች

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ኢንትራስ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖ ኢንስቲትዩት ግቢ የሚያሻግረው ድልድይ ላይ እንዳሉ ነበር ፍተሻ ሲደረግላቸው የነበረው። ተማሪዎቹን ሌላ ቦታ ላይ ፈትሸው ማሻገር ሲገባቸው ድልድዩ ላይ አስቁመው መፈተሻቸው ነው ከአይን እማኞች የተሰማው።

"ዩኒቨርስቲው ከሚገባው በላይ ተማሪዎች ድልድዩ ላይ ስለወጡ አደጋ መድረሱን እንደ ምክንያት መግለፁ ተገቢ አይደለም የዩኒቨርስቲው ህንፃ አስተዳደር አካላት ድልድዩ የሚችለዉን የጭነት መጠን ከግምት በማስገባት የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ ነበረባቸዉ" ሲሉ በአከባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እና የተማሪ ወላጆች ገልፀዋል።

በአደጋው የተደናገጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማው ህዝብ፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች በሀዋሳ መንገዶች ላይ ሁኔታውን በጭንቀት እና ሀዘን ውስጥ ሆነው ሲከታተሉ ውለዋል።

@Esat_tv9
@Esat_tv9
2.6K viewsDagi, edited  04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 07:31:41
1.9K viewsDagi, 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 07:31:41
1.8K viewsDagi, 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 07:31:40
1.5K viewsDagi, 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 21:59:49
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ የተመደቡ ተማሪዎች ለነገው ፈተና እንዲዘጋጁ አሳሰበ።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባሰራጨው መልዕክት ዋናው ግቢ የተመደቡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዛሬ ጠዋት በተፈጠረው አደጋ ምክንያት ለዛሬ የታቀዱትን ፈተናዎች መፈተን እንዳልቻሉ ገልጿል።

"በተከሰተው ያልተጠበቀ አደጋ በጣም አዝነናል " ያለው ተቋሙ ሌሎች በሁኔታው ተደናግጠው ከግቢ የወጡ ሆነ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደየነበሩበት እንዲመለሱና ለነገ ፈተና እንዲዘጋጁ አሳስቧል።

@Esat_tv9
@Esat_tv9
1.5K viewsDagi, edited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 11:44:49
የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ዋናውን ግቢ ከቴክኖ ግቢ የሚያገናኘዉ ድልድይ ተደርምሶ ተማሪዎች ላይ አደጋ መድረሱን ተመልክተናል!

ጉዳቱ ምን ያህል እንደሆነ ባይታውቅም ፣ የተጎዱ ተማሪዎች ወደ ሀዋሳ ረፈራል ሆስፒታል እና ወደ ተለያዩ የህክምና ተቋማት ለእርዳታ እየተወሰዱ እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@Esat_tv9
@Esat_tv9
1.5K viewsDagi, edited  08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 19:23:28
አሜሪካ በ30 የቻይና ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች!!

የዓለም አንደኛ እና ሁለተኛ ልዕለ ሀያል የሆኑት ሀገራት የሆኑት አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ጦርነት ከጀመሩ ቆይተዋል። ቻይና በወታደራዊ ቴክኖሎጂ በአሜሪካ ላይ የበላይነትን መውሰዷ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን እንዳሳሰበ ሮይተርስ ዘግቧል።

የአሜሪካ ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን ፓርቲ ሴናተሮች ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቻይና ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ሲወተውቱ ነበርም ተብሏል።በዚህም መሰረት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናውን ግዙፉ የሚሞሪ አምራች ኩባንያ የሆነው ያንትዝ ቴክኖሎጂ ኩባንያን ጨምሮ በ30 ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።

ዋሸንግተን ከዚህ በተጨማሪም የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለቻይና ወታደራዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የማይክሮ ቺፕስ ምርቶቻቸውን እንዳይሸጡም እገዳ ጥለዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላም የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እየሻከረ የመጣ ሲሆን በታይዋን ጉዳይ ወደ ጦርነት እንዳያመሩም ተሰግቷል። የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ቻይና ከአሜሪካ ጋር በወታደራዊ ደህንነት እና አየር ንብረት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ  ላለመስራት መወሰኗን አስታውቃለች።

አሜሪካ ቻይና ከሩሲያ እና ኢራን ጋር ባላት ግንኙነት ደስተኛ እንዳልሆነች የገለጸች ሲሆን በተለይም የሩሲያን ነዳጅ መግዛቷን እንድታቆም በመወትወት ላይም ትገኛለች።


@Esat_tv9
@Esat_tv9
1.4K viewsDagi, edited  16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ