Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ዝርዝር ዛሬ በፓርላማ በጸደቀው “የመኖሪያ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ዝርዝር

ዛሬ በፓርላማ በጸደቀው “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ” ከተዘረዘሩ ድንጋጌዎች ውስጥ፤ “የመኖሪያ ቤት የኪራይ ውል ዘመንን” የሚመለከቱት የሚጠቀሱ ናቸው። “የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም” ሲል የደነገገው አዋጁ፤ ይህ የተደረገበትን ዋነኛ ምክንያት በማብራሪያው ላይ አስፍሯል።

“የአዋጁ ዓላማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ በመሆኑ፤ ውሉ ከሁለት ዓመት ያነሰ ቢሆን አከራዩ ውሉን ለማደስ ፍቃደኛ ላይሆን ስለሚችል፤ ተከራይ በየጊዜው በቀጣይ ስለሚከራየው ቤት በመጨነቅ የተረጋጋ ህይወት እንዳይመራ ያደርገዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ አትቷል።

“ከሁለት ዓመት ያለፈ ዘመን ይኑረው ቢባል ደግሞ የአከራይን መብት እንዳይጫን፤ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የውል ዘመኑ ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ እንዲሆን” መደረጉን የአዋጁ ማብራሪያ አስገንዝቧል።

“አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ከሁለት ዓመት በታች የተደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች ላይ ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይሆን፤ በውላቸው ላይ ያጸደቁት ቤት ኪራይ የውል ዘመን ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደርጓል” ሲል ማብራሪያው አክሏል። ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ።

Via Ethiopia Insider

@Esat_tv1
@Esat_tv1