Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረ ◉በአዲሱ መመሪያ መመሪያ 34 | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረ

◉በአዲሱ መመሪያ መመሪያ 34 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ተደርጓል 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የቤት ሽያጭ ዋጋ ማሻሻያ ላይ ከሕብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች በመቅረባቸው፣ መመሪያው በድጋሚ እንዲከለስ ተደርጓል። 

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም  በተሠራጨው አዲስ መመሪያ በኮንዶሚኒየም ቤቶች እና በአፓርታማዎች ሽያጭ የካሬ ሜትር ዋጋ ላይ በአማካኝ 34 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።

የከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በጋራ ባካሄዱት ጥናት የተዘጋጀው ማኑዋል በቤት ሽያጭ ገቢ ላይ የዋጋ ቅናሽ እንዲያመጣ ተደርጓል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፋወሰን ደሲሳ ፊርማ ለሁሉም ክፍለ ከተሞች በተሰራጨው መመሪያ  እንደተመለከተው፣ ከዚህ በፊት በነበረው አሠራር ለአብነት ደረጃ አንድ በተባሉ አካባቢዎች የሚሸጥ የአንድ አፓርታማ ቤት  ዋጋ በካሬ ሜትር 132,200 ብር፣ በተመሳሳይ በዚሁ ደረጃ አንድ አካባቢ የኮንዶሚንየም ቤቶች ሽያጭ ዋጋ ደግሞ በካሬ ሜትር  72,300 ብር በሚል ቁርጥ ዋጋ ወጥቶላቸው የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ ማኑዋል ይህ ቁርጥ ዋጋ በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

የከተማው አስተዳደር የቤት ሽያጭ ግብይት ላይ አዲስ ማንዋል ለማውጣት የተገደደው፣  በግብይት ወቅት መሬት ላይ ያለው ዕውነታና የሚቀርበው የሽያጭ ውል እጅግ የተራራቀ በመሆኑ ነው ተብሏል። በቤት ግብይት ዙሪያ አሳንሶ መዋዋል፣ አሳንሶ መገመት፣ የስም ዝውውር ማዘግየትና ሌሎችም ተጠቃሽ ችግሮች መሆናቸው ተመልክቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1